የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

የቼክ ሪፐብሊክ ‘ዜቶር (ZETOR)’ ትራክተሮች ዛሬም በገበያ ላይ ናቸው

EABC & EIH Sign Shareholders Agreement with Asset Green Company

ኮርፖሬሽኑ በቦንጋ ያስገነባው የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ተመረቀ

ኮርፖሬሽኑ በጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት እውቅና አገኘ

የኮርፖሬሽኑ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ

የኮካ እርሻ ልማት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20/2017 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን ኮካ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተረከበውን 5 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት የሚያስችለውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራ ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀመረ።
በልማት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ የምዕራብ ኦሞ ዞን፣ የማጂና ሱሪ ወረዳዎች አመራሮች እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ ተወካይ ተገኝተዋል።
ኮርፖሬሽኑ ኮካ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በተረከበው መሬት ምርጥ ዘር እንደሚያባዛ እና ወደ ውጭ የሚላኩ ሰብሎችን እንደሚያመርት መገለጹ ይታወሳል።
ሦስተኛ የልማት መዳረሻው ከሆነው የኮካ እርሻ መሬት ልማት በተጨማሪ በክልሉ የታማሻሎ የምርጥ ዘር ማባዣ እርሻ ልማት እና በቅርቡ እንደሚመረቅ የሚጠበቀውን የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓት እና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ፕሮጀክት እያስተዳደረ ይገኛል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

ኮርፖሬሽኑ በትግራይ ክልል በጦርነት ፈርሰው የነበሩ የመማሪያ ክፍሎችን ገንብቶ አስመረቀ

EABC receives walking tractors

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የልዑካን ቡድን የኮርፖሬሽኑን የምርጥ ዘር እርሻዎች ጎበኘ

EABC earns 846 thousand USD from exporting incense & gum