አዲስአበባ፣ጥቅምት 30/ 2016 ዓ.ም. (ኢግሥኮ)፡- በአፈር ማዳበሪያ ግዥ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ለውጥ በመደረጉ ማዳበሪያ በመጠን፣ በጥራት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በጊዜ ለመግዛት እና ለማጓጓዝ መቻሉን የግብርና ሚኒስትሩ ገለጹ። ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ይህን የገለጹት በአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እና ሥርጭት ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና መፍትሔዎች ዙሪያ በአዳማ ኃይሌ ሪዞርት ሆቴል ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ነው፡፡በግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ትብብር በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደተናገሩት፣ የማዳበሪያ ጉዳይ የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ የአስፈጻሚዎችን አርበኝነት ይጠይቃል ብለዋል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በማዳበሪያ አቅርቦት እና ሥርጭት ላይ ተዋንያን የሆኑ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ተናበው በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ከዚህ በኋላ መንግሥት በማዳበሪያ ሥርጭት ላይ ምንም አይነት የአፈጻጸም ክፍተት አይታገስም ያሉት አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የ2016/17 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ እስከ ግንቦት ወይም ሰኔ 2016 ዓ.ም ድረስ ተጓጉዞ እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል። የማዳበረያ ግዥ መጓተትን ለመፍታት ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሥራ ላይ የነበረው የግዥ መመሪያ እንዲቀየር መደረጉን እና አሁን ላይ ማዳበሪያ ከአምራቾች በቀጥታ ግዥ፣ በውስን ጨረታ እና የመንግሥት ለመንግሥት ግዥ መፈጸም የሚቻልበት አሠራር መዘርጋቱን የተናገሩት ደግሞ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ቀድሞ በነበረው የአፈር ማዳበሪያ የግዥ ሥርዓት መሰረት የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጨረታ ሥራውን ካከናወነ በኋላ የግብርና ሚኒስቴር ግዥውን ያጸድቅ እንደነበረና ይህም መጓተትን ፈጥሮ መቆየቱን አስታውሰዋል። አክለውም አዲሱ የግዥ መመሪያ የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ በግዥው ላይ ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ዕድል የሚሰጠው መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በአጠቃላይ በአፈር ማዳበሪያ ግዥ ላይ ከፍተኛ ለውጥ በመደረጉ ከግዥ ጋር የተያያዙ ችግሮች መፈታታቸው እና በዚህም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የአፈር ማዳበሪያን ቀደም ብሎ መግዛት እና ማጓጓዝ መጀመሩን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የ2015/16 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ሥርጭት አፈጻጸም እንዲሁም የ2016/17 የማዳበሪያ ግዥና ሥርጭት ያለበት ደረጃን በተመለከተ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንት እና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ገለጻ ቀርቧል። በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ውይይቱን ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና አለሙ ስሜ (ዶ/ር) መርተውታል። በወቅቱ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም ምላሽ ሰጥተዋል። በውይይቱ የግብርና ሚኒስቴር እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፤ የክልል ግብርና እና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች፤ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ትብብር በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደተናገሩት፣ የማዳበሪያ ጉዳይ የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ የአስፈጻሚዎችን አርበኝነት ይጠይቃል ብለዋል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በማዳበሪያ አቅርቦት እና ሥርጭት ላይ ተዋንያን የሆኑ የፌዴራልና የክልል ተቋማት ተናበው በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ከዚህ በኋላ መንግሥት በማዳበሪያ ሥርጭት ላይ ምንም አይነት የአፈጻጸም ክፍተት አይታገስም ያሉት አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የ2016/17 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ እስከ ግንቦት ወይም ሰኔ 2016 ዓ.ም ድረስ ተጓጉዞ እንደሚጠናቀቅ አስታውቀዋል። የማዳበረያ ግዥ መጓተትን ለመፍታት ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሥራ ላይ የነበረው የግዥ መመሪያ እንዲቀየር መደረጉን እና አሁን ላይ ማዳበሪያ ከአምራቾች በቀጥታ ግዥ፣ በውስን ጨረታ እና የመንግሥት ለመንግሥት ግዥ መፈጸም የሚቻልበት አሠራር መዘርጋቱን የተናገሩት ደግሞ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ቀድሞ በነበረው የአፈር ማዳበሪያ የግዥ ሥርዓት መሰረት የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጨረታ ሥራውን ካከናወነ በኋላ የግብርና ሚኒስቴር ግዥውን ያጸድቅ እንደነበረና ይህም መጓተትን ፈጥሮ መቆየቱን አስታውሰዋል። አክለውም አዲሱ የግዥ መመሪያ የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ በግዥው ላይ ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ዕድል የሚሰጠው መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በአጠቃላይ በአፈር ማዳበሪያ ግዥ ላይ ከፍተኛ ለውጥ በመደረጉ ከግዥ ጋር የተያያዙ ችግሮች መፈታታቸው እና በዚህም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የአፈር ማዳበሪያን ቀደም ብሎ መግዛት እና ማጓጓዝ መጀመሩን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የ2015/16 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ሥርጭት አፈጻጸም እንዲሁም የ2016/17 የማዳበሪያ ግዥና ሥርጭት ያለበት ደረጃን በተመለከተ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንት እና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ገለጻ ቀርቧል። በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ውይይቱን ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና አለሙ ስሜ (ዶ/ር) መርተውታል። በወቅቱ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም ምላሽ ሰጥተዋል። በውይይቱ የግብርና ሚኒስቴር እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፤ የክልል ግብርና እና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች፤ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡