አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!” በሚል መሪ ቃል 19ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም በዋና መ/ቤት አከበሩ፡፡
ቀኑን በማስመልከት መልእክት ያስተላለፉት የኮርፖሬሽኑ የግብርና ግብዓት ምርትና አቅርቦት ዐቢይ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ጠምስ፣ የሰንደቅ ዓላማ ቀን፥ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ኮርፖሬሽኑ በመንግሥት የተሰጠውን ተልዕኮና አደራ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ በመደመርና በግምባር ቀደምነት እንዲያሳካ የተቋሙ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ቃል የሚገቡበት ታሪካዊ ቀን መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በዕለቱ በተፈጸመው ቃለ መሀላ፣ የኮርፖሬሽኑ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በአንድነትና በጋራ ስሜት አብሮ በመቆም በበጀት ዓመቱ በመንግሥት ትኩረት አግኝተው የታቀዱ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን ለማሳካት በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃል ገብተዋል፡፡
###
ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!


