አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ግብርናን በማዘመን ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) በክቡራን ደንበኞቹ ፍላጎት መሰረት ጥራት ያላቸውን ተጨማሪ የስንዴና በቆሎ አጭዶ መውቂያዎችን (Combine harvesters) በብዛት ማስመጣቱን ሲገልጽ በከፍተኛ ደስታ ነው።
የእርሻና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አምራች ከሆነው ታዋቂው የቻይናው ዙምላየን ኩባንያ ከእነመለዋወጫቸው ያስመጣቸው እነዚህ አጭዶ መውቂያዎች ዋጋቸው ተመጣጣኝ ሲሆን፣ ለአያያዝና አጠቃቀም ምቹ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም የተጠቀሟቸው ደንበኞች ይመሰክራሉ።
በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ የስንዴ፣ ገብስ፣ ማሽላ፣ ባቄላ፣ ሽንብራና ምስር ቆሞ መውቂያዎችን (Multi-Crop Threshers) ከቱርክ ሀገር ከእነመለዋወጫቸው በማስመጣት ለተጠቃሚዎች ማቅረቡን ሲያበስር ማሽኖቹ በዘርፉ የሚኖራቸውን ውጤታማነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
ከሽያጭ በኋላ የቴክኒክ ሞያ ሥልጠና፣ የጥገና እና የምክር አገልግሎቶችን ለደንበኞች ስለምንሰጥ በአጠቃቀምና በጥገና ዙሪያ ሀሳብዎን እኛ ላይ ይጣሉ።
እርስዎ ሁሉ ሙሉ፣ ሁሌም ዝግጁ ወደ ሆነው ኮርፖሬሽናችን ጎራ ይበሉ፤ በአገልግሎታችን ተደስተው ይመለሳሉ።
ለበለጠ መረጃ:- +0114 423 438 ወይም 0911 157 091 ወይም 0911 433 489 ላይ ይደውሉ።








###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን