የኮርፖሬሽኑ የሩብ ዓመት አፈጻጸም ተገመገመ
- አፈጻጸሙ ካለፉት ሦስት ዓመታት አማካይና ከ2018 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነጻጸር ብልጫ አለው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ተገመገመ።
የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም ከ2016፣ 2017 እና 2018 በጀት ዓመታት አማካይ እና ከ2018 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነጻጸር በኦፕሬሽን ሥራዎች፣ በገቢና ትርፍ ከፍተኛ ብልጫ ማሳየቱ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል።
ከግብርና ግብዓት፣ ከምግብ እህል እና ከእርሻ መሣሪያዎች አቅርቦት እንዲሁም ከሪፎርም እና ከእርሻ ሥራዎች አኳያም የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡ እና የሽያጭ አፈጻጸምም አበረታች መሆኑ ተገልጿል።
ግምገማውን የመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ፣ በሩብ ዓመቱ የተገኘውን ውጤት አድንቀው፣ በቀጣይ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በላቀ ደረጃ ለማሳካት ከተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የበለጠ ውጤት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
አክለውም ማኅበረሰቡን ለሚጠቅሙና ለኮርፖሬሽኑ ተጨማሪ ገቢን ለሚያስገኙ የምግብ እህል፣ የእንስሳት እርባታ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እና የማር ምርት ከፍተኛ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ለግብዓት አቅርቦት፣ ለሪፎርም ሥራዎች፣ ለወጪ ቅነሳ፣ ለፕሮጀክት አስተዳደር፣ ለአርፒ፣ ለግዥና ሽያጭ ሥራዎች ትኩረት ሰጥቶ ውጤት ማምጣት እንደሚገባ አስታውቀዋል።
ለሦስት ቀናት በተደረገው የሩብ ዓመት ግምገማ ላይ የማኔጅመንት አባላት፣ የቅርንጫፍና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ የመሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበር አመራሮችና የቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!




















