አዲስ አበባ፣ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራሮች ከቻይና መንግሥታዊ የግብርና መሣሪያዎች አምራችና አቅራቢ ድርጅት – ‘ሎቮል’ – Lovol የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ትብብር አብሮ መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም በተቋሙ ዋና መ/ቤት ተወያዩ።

‘ሎቮል’ – Lovol ተብሎ የሚታወቀው ኩባንያ በቻይና ቀዳሚ የእርሻ መሣሪያዎች አምራች እንደሆነ እና ከ120 በላይ የዓለም ሀገራት ምርቶቹን እንደሚያቀርብ በውይይቱ ተጠቁሟል።

በወቅቱ የ’ሎቮል’ ስሪት የሆኑ ዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎችን እና ቴክኖሎጂዎችን በኮርፖሬሽኑ በኩል ለአርሶ አደሩና ለተለያዩ ተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ በሚቻልባቸው እድሎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

በዕለቱ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይና ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደሳለኝ በላቸው እና ሌሎች የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም በ’ሎቮል’ በኩል የኩባንያው የአፍሪካና የኢትዮጵያ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
               ###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!