ክቡራን ደንበኞቻችን፣
በግብርናው ዘርፍ የደንበኞቹን ፍላጎት በማርካት የሚታወቀው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ እነሆ በከፍተኛ ፍጥነት አጭዶ፣ ወቅቶና አበጥሮ ለጎተራ የሚያበቃውን ዘመናዊ “Zoomlion TE100 PRO” የሰብል መሰብሰቢያ ማሽን (Combine Harvester) ይዞላችሁ ቀርቧል።
የእህል ብክነትን በመቀነስ፣ ጊዜንና ወጪን በመቆጠብ የተመሰከረለት ይህ 190 የፈረስ ጉልበት ያለው ማሽን፣ በሰከንድ 10 ኪሎ ግራም ሰብል አጭዶ፣ ወቅቶና አበጥሮ ለጎተራ ያዘጋጃል።
ስለ ነዳጅ አያስቡ! ዙም ላየን 400 ሊትር ነዳጅ ከመያዝ አቅሙ ባሻገር በነዳጅ ቆጣቢነቱም በተጠቃሚዎቹ ዘንድ ይታወቃል።
ስንዴ ፣ በቆሎና አኩሪ አተር አጭዶ፣ ወቅቶና አበጥሮ ለጎተራ የሚያበቃው ይህ ማሽን፣ 450 ሚሊ ሜትር ከመሬት ከፍ (Ground Clearance) ስለሚል ረግረጋማ፣ ጭቃማና ያልተስተካከሉ የእርሻ መሬቶችን በቀላሉ ይሻገራል።
ስለ መለዋወጫ አያስቡ፤ ሁሌ ሙሉ፤ ሁሌም ዝግጁ ወደ ሆነው ተቋማችን ጎራ ሲሉ በቂና አስተማማኝ መለዋወጫዎችን ያገኛሉ።
እንግዲያውስ ምን ይጠብቃሉ? ዋስትናውን እኛ ላይ በመጣል የሥራዎን ድካም የሚቀንስልዎትንና ጊዜና ወጪዎን የሚቆጥበውን ዙም ላየን ኮምባይን ሀርቨስተር ዛሬውኑ በመግዛት ትርፋማ ይሁኑ!
አድራሻ:- ሳሪስ ወደ ቃሊቲ በሚወስደው ዋና መንገድ ከፋፋ የምግብ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር ጀርባ ወይም ከኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ወረድ ብሎ
ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር +251911 433 489 ወይም +251911 157 091 ላይ ይደውሉ።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን




