የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

የሠራተኞች ዓመታዊ በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዓመታዊ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ተከበረ።

በዚህ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ የ2018 በጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑን ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግሩ መሠረቶች የተጣሉበት ዓመት መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በተቋሙ አሠራር፣ አደረጃጀት፣ በንብረት አስተዳደርና አያያዝ አዎንታዊ ለውጦች መደረጋቸውን አብራርተዋል።

በበጀት ዓመቱ በገቢና በትርፍ በኩል ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም መመዝገቡን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ አፈጻጸሙ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከተመዘገበው አፈጻጸም የላቀ መሆኑን አስታውቀዋል።

ለዚህ ስኬት መገኘት የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት፣ የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች፣ ደንበኞች እንዲሁም የሌሎች ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ርብርብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን በመጠቆም ምስጋና አቅርበዋል።

​የሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ዳንኤል ስለሺ በበኩላቸው፣ ቦርዱ ከኮርፖሬሽኑ አመራርና ሠራተኞች ጎን በመሆን ለአዎንታዊ ለውጦች መመዝገብ የድርሻውን መወጣቱን ገልጸው፣ በቀጣይም አስፈላጊው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የመሠረታዊ ሠራተኞች ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ ደበሌ በበጀት ዓመቱ አመራሩና ሠራተኛው በመተባበር ላስመዘገቡት ውጤት ምስጋና አቅርበው፤ በቀጣይም እያንዳንዱ ሠራተኛ በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በብቃት በመወጣት ለጋራ ስኬት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።

​በዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይ ለተቋሙ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ኮርፖሬሽኑን ለበርካታ ዓመታት አገልግለው በጡረታ ለተሰናበቱ አመራሮችና ሠራተኞች የምስጋና እና የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር)፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መለሰ መና እና የኮሚቴው አባላት እንዲሁም የኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮሌኔል ሸጋው ሙሉጌታ እና ሌሎች የባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ሰብሎችን ለ2018/19 ምርት ዘመን በብዛትና በጥራት ለሽያጭ ያቀረበ ሲሆን ክቡራን ደንበኞቻችን ከዚህ በታች በተዘራዘሩት አድራሻዎች የሚትፋልጉትን ዘር በግዥ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሰዉቃለን፡፡

🌱 የዘር ሽያጭ • 2018/19 የምርት ዘመን

የተለያዩ ሰብሎችና የበቆሎ ዘር ሽያጭ

የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በብዛትና በጥራት ያቀረባቸውን የተለያዩ የሰብል ዘሮች እና የበቆሎ ዝርያዎች ለደንበኞች ያቀርባል። ግዥ ለማከናወን ከታች በተጠቀሱት ቅርንጫፍ/ቅ/ጽ/ቤቶች ያነጋግሩ።

6የሽያጭ ቅርንጫፎች
12+የተለያዩ የሰብል አይነቶች
7የበቆሎ ዝርያዎች

የሽያጭ ቅርንጫፎች

የሚገኙበት ቅ/ጽ/ቤት እና የመገኛ ስልክ ቁጥሮች።

ሃዋሳ

☎ 965245703 / 913096336
1

ነቀምቴ

☎ 986533838
2

ኮፈሌ

☎ 911984706 / 0910037541
3

አሰላ

☎ 911909095 / 0968170677
4

ባህር ዳር

☎ 918340006
5

ቦንጋ

☎ 917018334
6

የሰብል ዘር የመሸጫ ዋጋ

ሰብልየጥቅል መጠንየመሸጫ ዋጋዋጋ በኩንታልአስተያየት
ገብስ (የምግብና የቢራ) ሁሉም ዝርያዎች62.5 kg8,125 ብር13,000 ብር
ጤፍ ሁሉም ዝርያዎች15 kg2,653.5 ብር17,690 ብር
ማሽላ20 kg2,120 ብር10,600 ብር
ሩዝ ሁሉም ዝርያዎች25 kg2,660 ብር10,640 ብር
ዳጉሳ ሁሉም ዝርያዎች15 kg1,260 ብር8,400 ብር
ባቄላ ሁሉም ዝርያዎች50 kg7,600 ብር15,200 ብር
አተር ሁሉም ዝርያዎች50 kg9,050 ብር18,100 ብር
ሽምቡራ ሁሉም ዝርያዎች25 kg4,475 ብር17,900 ብር
ምስር ሁሉም ዝርያዎች20 kg4,432 ብር22,160 ብር
ተልባ ሁሉም ዝርያዎች20 kg4,200 ብር21,000 ብር
ጎማን ሁሉም ዝርያዎች25 kg4,300 ብር17,200 ብር
ሱፍ ሁሉም ዝርያዎች10 kg2,050 ብር20,500 ብር
ስንዴ ሁሉም ዝርያዎች50 kg5,550 ብር11,100 ብርአሮሚያ፤ ኢግስኮ፤ደቡብ፤ማዕከለዊና ሶማሌ
ስንዴ ሁሉም ዝርያዎች50 kg6,350 ብር12,700 ብርትግራ፤አማራና ኢግስኮ

የበቆሎ ዘር ዝርያዎች

በቅርንጫፍ መሠረት የተዘረዘሩ ዝርያዎችና የመሸጫ ዋጋዎች።

ሃዋሳ☎ 913096336
7 ዝርያዎች
የበቆሎ ዝርያለ0.5 ሄ/ር — 12.5 ኪ.ግለ4 ሄ/ር — 100 ኪ.ግ
BH-5461,625 ብር13,000 ብር
BH-5471,625 ብር13,000 ብር
BH-5491,937.5 ብር15,500 ብር
ጊቤ-21,237.5 ብር9,900 ብር
መልካሳ-21,237.5 ብር9,900 ብር
ሀዋሳ-11,650 ብር13,200 ብር
ነቀምቴ☎ 986533838 / 917817812
7 ዝርያዎች
የበቆሎ ዝርያለ0.5 ሄ/ር — 12.5 ኪ.ግለ4 ሄ/ር — 100 ኪ.ግ
BH-6611,562.5 ብር12,500 ብር
BH-5461,625.5 ብር13,000 ብር
BH-5471,625.5 ብር13,000 ብር
BH-5491,937.5 ብር15,500 ብር
ጊቤ-21,237.5 ብር9,900 ብር
መልካሳ-21,237.5 ብር9,900 ብር
ሀዋሳ-11,650 ብር13,200 ብር
ኮፈሌ☎ 911984706 / 910037541
7 ዝርያዎች
የበቆሎ ዝርያለ0.5 ሄ/ር — 12.5 ኪ.ግለ4 ሄ/ር — 100 ኪ.ግ
BH-6611,562.5 ብር12,500 ብር
BH-5461,625 ብር13,000 ብር
BH-5471,625.5 ብር13,000 ብር
BH-5491,937.5 ብር15,500 ብር
ጊቤ-21,237.5 ብር9,900 ብር
መልካሳ-21,237.5 ብር9,900 ብር
ሀዋሳ-11,650 ብር13,200 ብር
አሰላ☎ 911909095 / 968170677
7 ዝርያዎች
የበቆሎ ዝርያለ0.5 ሄ/ር — 12.5 ኪ.ግለ4 ሄ/ር — 100 ኪ.ግ
BH-6611,562.5 ብር12,500 ብር
BH-5461,625 ብር13,000 ብር
BH-5471,625.5 ብር13,000 ብር
BH-5491,937.5 ብር15,500 ብር
መልካሳ-21,237.5 ብር9,900 ብር
ጊቤ-21,237.5 ብር9,900 ብር
ሃዋሳ-11,650 ብር13,200 ብር
ባህር ዳር☎ 918340006 / 920762583
7 ዝርያዎች
የበቆሎ ዝርያለ0.5 ሄ/ር — 12.5 ኪ.ግለ4 ሄ/ር — 100 ኪ.ግ
BH-6611,500 ብር12,000 ብር
BH-5461,600 ብር12,800 ብር
BH-5471,625.5 ብር13,000 ብር
BH-5491,937.5 ብር15,500 ብር
መልካሳ-21,237.5 ብር9,900 ብር
ጊቤ-21,237.5 ብር9,900 ብር
ሃዋሳ-11,650 ብር13,200 ብር
ቦንጋ☎ 0937276513 ወይም / 917018334
7 ዝርያዎች
የበቆሎ ዝርያለ0.5 ሄ/ር — 12.5 ኪ.ግለ4 ሄ/ር — 100 ኪ.ግ
BH-6611,562.5 ብር12,500 ብር
BH-5461,625 ብር13,000 ብር
BH-5471,625.5 ብር13,000 ብር
BH-5491,937.5 ብር15,500 ብር
መልካሳ-21,237.5 ብር9,900 ብር
ጊቤ-21,237.5 ብር9,900 ብር
ሃዋሳ-11,650 ብር13,200 ብር

የኮርፖሬሽኑ አፈጻጸም ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ከፍተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) ገለጸ።

የኮርፖሬሽኑ አፈጻጸም ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በተገመገመበት ወቅት፣ ተቋሙ ያስመዘገበው አፈጻጸም ከፍተኛ መሆኑን የሆልዲንጉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል አስታውቀዋል።

የኮርፖሬሽኑ አዲሱ አመራር በኃላፊነት በመሥራቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ሊያመጣ ችሏል ያሉት አቶ ሀብታሙ፣ የተቋሙን ገጽታ በመጠበቅና ልማቱን በማስቀጠል በኦፕሬሽን፣ በፋይናንስና በማኅበራዊ ኃላፊነት ያስመዘገበውን ከፍተኛ ውጤት ኢኢሆ ያደንቃል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ከ438 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ያመረተ ሲሆን፣ ከ20.8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል።

በፋይናንስ ረገድም፣ የኮርፖሬሽኑ የ2018 በጀት ዓመት ገቢና ትርፍ ካለፉት ሦስት ዓመታት (ከ2015-2017) ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ የ15.3 ቢሊዮን ብር ገቢና የ3.6 ቢሊየን ብር ትርፍ ተመዝግቧል።
               ###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

የኮፈሌ ቅርንጫፍ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ሽያጭ አከናወነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮፈሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ዘርና የምግብ እህል ለአርሶ አደሮችና ሌሎች ተጠቃሚዎች መሸጡን ገለጸ።

​የጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቡሽራ መሐመድ እንደገለጹት፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በበጀት አመቱ ከ1.4 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን 58 ሺህ 884 ኩንታል ምርጥ ዘርና 49 ሺህ 50 ኩንታል የምግብ እህል ለገበያ አቅርቧል።

​በተጨማሪም ቅርንጫፉ በኮፈሌ ከተማ ባለው የዘር ማበጠሪያና ማዘጋጃ ማዕከል 55 ሺህ 737 ኩንታል ዘር አበጥሮ በማዘጋጀት ለአርሶ አደሮች ማቅረቡን ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል በበጀት ዓመቱ በኮንትራት እርሻ በተለይም በባሌ ዞኖች በሚገኙ ሰፋፊ የመንግሥትና የባለሀብት እርሻዎች 6 ሺህ 244 ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን ከ155 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት በትብብር መመረቱን አቶ ቡሽራ ተናግረዋል።

የቅርንጫፉ የዘር አቅርቦት በኮፈሌ፣ ዶዶላ፣ ገደብ አሳሳ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌና በባሌ ዞን አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮችንና ሌሎች ተጠቃሚዎችን ተደራሽ ያደርጋል።

​በ1971 ዓ.ም የተቋቋመው የኮፈሌ ቅርንጫፍ፣ ከኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አንጋፋ ቅርንጫፎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በዋናነት በምርጥ ዘር ምርት፣ ዝግጅትና አቅርቦት ሥራ ላይ ተሰማርቶ እየሠራ ይገኛል።
              ###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

ማስታወቂያ

ስለ እኛ

ስለ እኛ

ኢግሥኮ ምን ዓላማዎችን እንዲያሳካ ተቋቋመ? ምርትና አገልግሎቶቹ ምንድናቸው? የእስካሁኑ የልማት ጉዞው ምን ይመስላል?

ተከታዩ ፕሮፋይል ይህንኑ በአጭሩ ያስቃኛል።

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) – አጭር መግለጫ/ፕሮፋይል

ምስረታ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) በግብርናው ዘርፍ ከ30 እስከ 40 ዓመት ድረስ በተናጠል አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ አምስት ነባር ድርጅቶችን (የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት፣ የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት፣ የእርሻ መሣሪያዎችና የቴክኒክ አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ድርጅት እና የተፈጥሮ ሙጫ ምርትና ገበያ ድርጅት) በማዋሃድ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 368/2008 መሠረት ታህሳስ 2008 ዓ.ም የተቋቋመ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ነው፡፡

ተጠሪነት

በግሉ ዘርፍና በተደራጁ ማኅበራት የማይሸፈኑ የገበያ ክፍተቶች ውስጥ የድርሻውን በመውሰድ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ የሚገኘው ኮርፖሬሽኑ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሲሆን፣ በሥራ አመራር ቦርድ ይመራል፡፡

የተቋቋመበት ዓላማ

የተቋቋመበት ዓላማ ለግብርና ምርትና ምርታማነት ዕድገት አስተዋጽዖ የሚያደርጉ እና ለዘመናዊ እርሻና ለአግሮ ኢንዱስትሪ መስፋፋት መሠረት የሚሆኑ ቴክኖሎጂዎችን እና ግብዓቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ በማድረግ ሀገራዊ ልማትና ዕድገትን ለማፋጠን ነው፡፡

የተቋቋመበት ዝርዝር ዓላማዎቹም የሚከተሉት ናቸው፦

  1. የግብርና ምርት ማሳደጊያዎችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ገዝቶ ለገበያ ማቅረብ፤ ማዘጋጀት፤ የግብርና ምርት ማሳደጊያዎችን የገበያ ዋጋ የማረጋጋት ተግባራትን ማከናወን፤
  2. የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት፣ የእርሻና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን የጥገና አገልግሎት፣ የእርሻ መሣሪያዎችንና የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን የኪራይ አገልግሎት በክፍያ መስጠት፤
  3. የእርሻ መሣሪያዎችንና መለዋወጫዎችን፣ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን እና አግሮ ኬሚካሎችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ገዝቶ ለሽያጭ ማቅረብ፤
  4. ዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎች አጠቃቀም እንዲለመድ አስፈላጊውን ትምህርት መስጠት፤ ስለ እርሻ መሣሪያዎች አያያዝና አጠቃቀም የምክር አገልግልት መስጠት፤ የቴክኒክ ሞያ ማሻሻያ ሥራ ላይ ሥልጠና መስጠት፤
  5. የተፈጥሮ ሙጫ ምርት መሰብሰብ፣ መግዛት፣ እሴት መጨመር፣ ማዘጋጀት፤ ሌሎች ከደን ውጤቶች የሚመረቱ ምርቶችን ማምረት፣ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያዎች ማቅረብ፤
  6. የእርሻ መሬት ልማት ጥናትና ዲዛይን፣ የእርሻ መሬት ቅየሳ፣ ምንጣሮና ማስተካከል፣ የውኃ ተፋሰስና የመስኖ ሥራ እንዲሁም ከእርሻ መሬት ልማት ጋር የተዛመዱ ሥራዎችን ማከናወን፤
  7. የአዳዲስና ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን አዋጪነት ጥናት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣ የቴክኖሎጂ መረጣና ድርድር፣ የተከላና የኮሚሽኒንግ እንዲሁም የምርምር ሥራዎች እንዲካሄዱ ማድረግ፤
  8. አቅሙ ካላቸው የሀገር ውስጥ እና የውጪ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር የግብርና የማምረቻ መሣሪያዎችና መለዋወጫዎች ዲዛይንና የማምረት ሥራዎች በሀገር ውስጥ እንዲከናወኑ ማድረግ፤
  9. ለመስኩ የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በሚፈለገው ዓይነት፣ መጠንና ጥራት ለማፍራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው የትምህርት፣ የምርምርና የሥልጠና ተቋማት ጋር በመተባበር መሥራት፤
  10. በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሚሰጠው አቅጣጫ ላይ በመመስረት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ተወዳዳሪና አትራፊ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ እገዛ የሚያደርጉለትን የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂና የዘመናዊ አስተዳደር ግብዓቶችን ለማግኘት የሚያስችለውን (ኢንቨስትመንት መሳብንም ሆነ በኢንቨስትመንት መሳተፍን ጨምሮ) ጥናት በማካሄድ ሲፈቀድ ተግባራዊ ማድረግ፤
  11. የተለያዩ የአዝዕርት፣ የአትክልት፣ የፍራፍሬና የመሳሰሉት ቅድመ መሥራች፣ መሥራችና የተመሠከረለት ዘር ማባዛት፣ ማበጠርና ማዘጋጀት፣ እንደ አስፈላጊነቱም ቅድመ መሥራች ዘሮችን ከውጭ አገር በማስመጣት ማስመረት ወይም መሸጥ፣ ተረፈ ምርቶችን ለገበያ ማቅረብ፤
  12. በግብርና ግብዓት አቅርቦት፣ በእርሻ መሣሪያዎች አቅርቦት፣ በእርሻ መሣሪያዎች ጥገና፣ በተፈጥሮ ሙጫ ምርትና ገበያ፣ በሜካናይዜሽን አገልግሎትና በተዛማጅ ሥራዎች ዙሪያ ምርምር በማካሄድ የተሻሻሉትን ተግባራዊ ማድረግ፣ በውጤቱም ተወዳዳሪነትን ማረጋገጥ፤
  13. የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሚሠጠው አቅጣጫ መሠረት ቦንድ መሸጥ፣ ዋስትና ማስያዝ፣ ከሀገር ውስጥና ከውጪ የገንዘብ ምንጮች የብድር ውል መደራደርና ሲፈቀድ መፈራረም፤
  14. ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን ማከናወን ናቸው፡፡

የኮርፖሬሽኑ ተልዕኮ፣ ራዕይ እና እሴቶች

ተልዕኮ

ለግብርና ምርትና ምርታማነት ዕድገት አስተዋጽዖ የሚያደርጉ፣ ለዘመናዊ እርሻና ለአግሮ ኢንዱስትሪ መስፋፋት መሠረት የሚሆኑ ቴክኖሎጂዎችን እና ግብዓቶችን ተደራሽ በማድረግና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ሀገራዊ ልማትና ዕድገትን ማፋጠን፡፡

ራዕይ

በግብርና ግብዓት አቅርቦት እና በሜካናይዜሽን አገልግሎት በ2022 ዓ.ም በአፍሪካ ተወዳዳሪ ተቋም መሆን፡፡

እሴቶች

  • ተዓማኒነት
  • ግልጽነት
  • ቅንነት
  • ቁርጠኝነት
  • የጋራ ተጠቃሚነት
  • ማኅበራዊ ኃላፊነት

የአንድ መስኮት አገልግሎት

የአንድ መስኮት የተቀናጀ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ኮርፖሬሽኑ፣ በተቀናጀ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ከመሬት ዝግጅት እስከ ጎተራ የሚዘልቁ የግብርና ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ በተጨማሪም ለግብርና መዘመንና ለምርታማነት እድገት የላቀ አስተዋጽዖ ያላቸውን ግብዓቶች (ምርጥ ዘር፣ ጠጣርና ፈሳሽ ማዳበሪያዎች፣ አግሮኬሚካሎች) እንዲሁም የእርሻ መሣሪያዎችን ከእነተቀጽላቸው እና መለዋወጫቸው በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ያቀርባል፡፡

ከዚህ ባሻገር ኮርፖሬሽኑ ለደንበኞቹ እየሰጠ የሚገኘውን የአንድ መስኮት አገልግሎት የተሟላ ለማድረግ የምክር፣ የቴክኒክና ሞያ ሥልጠና፣ የዘር ብጠራ፣ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት እና የተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎቶችን በዋና መ/ቤት እና በቅርንጫፎች ተደራሽ በማድረግ ላይ ነው።

የግብርና ግብዓቶችና የእርሻ መሣሪያዎች አቅርቦት እና አገልግሎቶች

ምርጥ ዘር

በሀገር ደረጃ በምርጥ ዘር አቅርቦት ፋና ወጊ የሆነው ኮርፖሬሽኑ፣ በተለያዩ ክልሎች የራሱን ስድስት የምርጥ ዘር ማባዣ እርሻ ልማት ጣቢያዎችን በማቋቋም እንዲሁም በሰፋፊ የመንግሥትና የግል እርሻዎች እና በክላስተር በተደራጁ አርሶ አደሮች ማሳ በኮንትራት በመስራት በአጠቃላይ ከ20 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የ22 ሰብሎችን 90 ዝርያዎች እያባዛ በዓመት ከ450 ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ለተጠቃሚዎች እያቀረበ ይገኛል፡፡

ይህም በሀገር ደረጃ ካለው የምርጥ ዘር ፍላጎት ውስጥ 30 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ እንዲያሟላ አስችሎታል፡፡

በአጠቃላይ ኮርፖሬሽኑ በተለያዩ ክልሎች በአገኛቸው ተጨማሪ የእርሻ መሬቶች ዘር እያባዛ ሲሆን፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ሰብሎችን ለማምረትም ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ማዳበሪያ፣ አግሮኬሚካልና የእንስሳት መድኃኒት

ኮርፖሬሽኑ በሀገር ውስጥ ብቸኛ የጠጣር የአፈር ማዳበሪያ አስመጪ ሲሆን፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የአፈር ማዳበሪያዎች (በጠጣርና በፈሳሽ መልክ)፣ ጸረ አረም፣ ጸረ ነፍሳትና ጸረ ፈንገስ ኬሚካሎች እና የእንስሳት መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ ነው፡፡

የእርሻ መሣሪያዎች

ኮርፖሬሽኑ ለሀገሪቱ መልክአ ምድር እና የአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ዘመናዊና ጥራት ያላቸውን ትራክተሮችና ተቀጽላዎች/implements – ማረሻ፣ መከስከሻ፣ መስመር ማውጫ፣ ዘር መዝሪያ፣ ማዳበሪያ መበተኛ…/፣ ኮምባይን ሀርቨስተር፣ የኮንስትራክሽን እና የኬሚካል መርጫ መሣሪያዎችና መለዋወጫዎች፣ የመስኖ ፓምፕ ወዘተ ያቀርባል።

የሜካናይዜሽን አገልግሎት

የተቀናጀ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎትን በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ የሚታወቀው ኮርፖሬሽኑ በግብርናው ዘርፍ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮች፣ ባለሃብቶች፣ የልማት ድርጅቶች ወዘተ ከመሬት ዝግጅት እስከ ጎተራ የሚዘልቁ የግብርና ሥራዎችን ያከናውናል፡፡

የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል

ኮርፖሬሽኑ ለካፒታል ፕሮጀክት በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የዘር ማበጠሪያና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው ክልሎች የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ለማቋቋም እየሠራ ነው፡፡ ለአብነት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ የአስገነባውን ግዙፍ ማዕከል መጥቀስ ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ ይህን መሰል ማዕከል በሌሎች ክልሎችም ለማስፋፋት የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የእርሻ መሣሪያዎችን የመገጣጠም ሥራ

የግብርና ሜካናይዜሽንን በማስፋፋት ረገድ ኮርፖሬሽኑ አዳዲስ የእርሻ መሣሪያዎችን ታዋቂ ከሆኑ የአውሮፓ እና የቻይና አምራች ኩባንያዎች በማስመጣት እና ባለው ወርክሾፕ በሂደት ሙሉ በሙሉ ገጣጥሞ ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በሽርክና መሥራት የሚችልበትን ስምምነት እያደረገ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ተቋሙ የእርሻ መሣሪያዎችን በከፊል የመገጣጠም ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች

ኮርፖሬሽኑ የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች የሆኑትን ሙጫ፣ እጣን፣ ከርቤና አበከድ በማምረትና በግዥ በማሰባሰብ አበጥሮ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ጭምር በማቅረብ በዓመት በሚሊየን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ላይ ነው፡፡

ተቋሙ እነዚህን ምርቶች የሚሰበስበው በዘርፉ ከተሰማሩ ማኅበራትና ግለሰቦች በግዥ መልክ ሲሆን፣ ምርቶቹ በአብዛኛው በትግራይ፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች ቆላማ አካባቢዎች ይገኛሉ፡፡

የደረቅ ጭነት ትራንስፖርትና የተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎቶች

ኮርፖሬሽኑ ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማሰማራት ለውስጥ እና ለውጭ ደንበኞች የግብርና ግብዓቶችንና የእርሻ መሣሪያዎችን እንዲሁም ሌሎች የደረቅ ጭነቶችን የማጓጓዝ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

በሌላ በኩል ለውስጥ እንዲሁም ለተለያዩ የግልና የመንግሥት ተቋማት ደንበኞች የተሽከርካሪዎች የቅድመ መከላከል (Preventive Maintenance Service) እና የብልሽት ጥገና አገልግሎት (Maintenance Service) ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም ለከባድ እና ቀላል ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ ምርመራ/ቦሎ/ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

የዓመታዊ ሽያጭ፣ ትርፍና የተፈቀደ ካፒታል እድገት

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ዓመታት በሀገራዊ የግብርና ዘርፍ የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ እና ለሦስተኛ ጊዜ በአዘጋጀው የተቋሙ ስትራተጂክ ዕቅድ (ከ2016- 2020 ዓ.ም) እየተመራ ውጤትን መሰረት ያደረገ የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና ሥርዓትን (BSC) የለውጥ መሣሪያ አድርጎ ወደ ሥራ በመግባቱ፣ በየዓመቱ በIFRS ደረጃዎች መሰረት በወቅቱ ሒሳብ በመዝጋቱና በማስቀጠሉ እንዲሁም የISO 9001፡2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓትን በመተግበሩ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡

በዚህም ዓመታዊ ገቢውን ሲቋቋም ከነበረበት ከ1.4 ቢሊዮን ብር በ2016 በጀት ዓመት ወደ 10.76 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከታክስ በፊት ትርፉን ከ45.6 ሚሊዮን ብር በ2016 በጀት ዓመት ወደ 1.8 ቢሊዮን ብር ማሳደግ ችሏል፡፡

ከዚህ የተነሳ ኮርፖሬሽኑ በየዓመቱ ምርቱን እያሳደገ እና አገልግሎቶቹን ይበልጥ ተደራሽ እያደረገ በመቀጠሉ እንዲሁም ትርፋማ ሆኖ በመዝለቁ ምክንያት ሲቋቋም በመንግሥት የተፈቀደለትን 2.44 ቢሊዮን ብር ካፒታል በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በማሟላት አሁን ላይ የተፈቀደ ካፒታሉን ወደ 7 ቢሊዮን 564 ሚሊዮን ብር ማሳደግ ችሏል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎም የተቋሙን ካፒታል በድጋሚ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

ማኅበራዊ ኃላፊነት

ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ ኮርፖሬሽኑ በየዓመቱ በአማካይ ለ2500 ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ እድል እየፈጠረ ሲሆን፣ ከሚያገኘው ትርፍ ላይም በየዓመቱ ለማኅበራዊ አገልግሎት በጀት በመመደብ በምርጥ ዘር ማባዣ እርሻ ልማት አካባቢዎች ለሚገኘው ማኅበረሰብ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግሥት ለሚቀርብለት የተለያዩ የድጋፍ ጥሪዎች እና የስፖንሰርሺፕ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል፤ አሁንም ድጋፍ ማድረጉን ቀጥሏል፡፡

በዚህ መሰረት በበጎ አድራጎት ሥራዎች በእርሻ ልማቱ አካባቢዎች ለሚገኘው ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት በመገንባት፣ መብራት በማስገባት፣ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶች በማደስ፣ ለችግረኛ ቤተሰብ ልጆች የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን በመለገስ፣ መንገድ በመሥራት እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ችግኞችን በመትከል፣ ደም በመለገስ ወዘተ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡

በተመሳሳይ ለአካባቢው አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች በአምስት በመቶ የዋጋ ቅናሽ ምርጥ ዘር በማቅረብ ለአርሶና አርብቶ አደሩ ያለውን አለኝታነት በማረጋገጥ ላይ ይገኛል፡፡

እውቅና እና ሽልማት

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በሚያቀርባቸው የግብርና ግብዓቶችና በሚሰጣቸው የተቀናጁ አገልግሎቶች በገበያ ውስጥ ተመራጭ ስለመሆኑ የረጅም ዓመት ደንበኞቹ ምስክሮች ናቸው፡፡

ለዚህም እንደ ማሳያ በ2017 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈበት 12ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ውድድር ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተካሄደ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ የአድናቆት የምስክር ወረቀት/Honorary Certificate/ ማግኘቱን መጥቀስ ይቻላል፡፡

በተመሳሳይ ኮርፖሬሽኑ በግብርናው መስክ በአስመዘገበው አበረታች ውጤት የአቢሲኒያ ዓለም አቀፍ የጥራት ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኢንደስትሪ ሽልማት ካጫቸው ከ57 ሺህ በላይ አምራችና አገልግሎት ሰጪ የመንግሥት፣ የግል እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ውስጥ ከተመረጡ 50 ተቋማት አንዱ በመሆን መጋቢት 2015 ዓ.ም የመጀመሪያውን የኢንደስትሪ የከፍተኛ ክብር ሽልማት ተቀዳጅቷል፡፡

በተጨማሪም በታማኝ ግብር ከፋይነት ለሦስተኛ ጊዜ በፕላቲነም ደረጃ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እጅ ሽልማት ተቀብሏል፡፡

ከዚህ ባሻገር በ2015/16 የምርት ዘመን በሀገር አቀፍ ደረጃ በስንዴ ልማት ከሀገራዊ ፍላጎት እስከ ውጭ ገበያ አቅራቢነት በመሸጋገር ሂደት ለአበረከተው የላቀ አስተዋጽዖ እንዲሁም በ2016/17 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ግዥ፣ አቅርቦትና ሥርጭት እንዲሳለጥ ለተወጣው ከፍተኛ ድርሻ የእውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀቶችና ዋንጫ አግኝቷል፡፡

በሌላ በኩል የኮርፖሬሽኑ የወንዶች የመረብ ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በ2015 እና በ2017 ዓ.ም በአዘጋጀው የስፖርት ውድድር ሻምፒዮን በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

አደረጃጀት

የአርሶና አርብቶ አደሩ አለኝታ የሆነው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን /ኢግሥኮ/ በመንግሥት የተሰጠውን ተልዕኮ ከመወጣት አኳያ በአራት ኮርፖሬት ዘርፎች (ግብርና ግብዓት ምርትና አቅርቦት ዐቢይ ዘርፍ፣ እርሻ መሣሪያዎችና የግብርና ውጤቶች አቅርቦት ዐቢይ ዘርፍ፣ ኮርፖሬት የሀብት አመራር ዘርፍ እና ኮርፖሬት ፋይናንስ ዘርፍ)፣ ዓላማ አስፈጻሚ በሆኑ አምስት የኦፕሬሽን ዘርፎች፣ በ14 ድጋፍ ሰጪ የሥራ ሂደቶች እንዲሁም በበርካታ ቅርንጫፎችና ጣቢያዎች በተደራጀ መዋቅር ከ1,600 በላይ ቋሚና ኮንትራት ሠራተኞችን ይዞ ግብርናን ለማዘመን እየሠራ ይገኛል፡፡

የዘርፎች አድራሻ እና የሚሰጡት አገልግሎት

ምርጥ ዘር፣ የዘር ብጠራ አገልግሎት፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ አግሮኬሚካል፣ የእንስሳት መድኃኒትና የኬሚካል መርጫ መሣሪያዎች ካስፈለግዎ

የግብርና ግብዓት ምርትና አቅርቦት ዐቢይ ዘርፍ

ስልክ፡- +251-11-440-3610
ፋክስ፡- +251-11-442-3613

ለምርጥ ዘር አንዲሁም ለዘር ብጠራ አገልግሎት

የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ

ስልክ፡- +251-11-661-2266
ፋክስ፡- +251-11-618-6123

ለአፈር ማዳበሪያ፣ አግሮኬሚካል፣ እንስሳት መድኃኒትና የኬሚካል መርጫ መሣሪያዎች

የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ

ስልክ፡- +251-11-442-5623/28
ፋክስ፡- +251-11-442-5622

የእርሻ መሣሪያዎች፣ የጭነት ተሽከርካሪዎችና ጥገና፣ የግብርና ውጤቶች ሽያጭና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ቢያስፈለግዎ

የእርሻ መሣሪያዎችና የግብርና ውጤቶች አቅርቦት ዐቢይ ዘርፍ

ስልክ፡- +251-11-442-5012

ለአስተማማኝና ዘመናዊ የእርሻና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ሽያጭና ኪራይ፣ መለዋወጫ እንዲሁም የቴክኒክ ሥልጠና አገልግሎት

የእርሻ መሣሪያዎች አቅርቦት ዘርፍ

ስልክ፡- +251-11-442-3438
ፋክስ፡- +251-11-442-0895

ለመሬት ዝግጅት፣ ምንጣሮ፣ መሬት ድልዳሎ፣ ለእርሻ ሥራ፣ ሰብል ለመሰብሰብና ለመውቃት እንዲሁም ለዕጣን፣ ሙጫ፣ ከርቤና አበከድ አቅርቦት

የግብርና ውጤቶች ሽያጭና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ

ስልክ፡- +251-11-442-5012

ለደረቅ ጭነት አገልግሎት እንዲሁም ለእርሻ መሣሪያዎችና የቀላል ተሽከርካሪዎች ጥገና

የተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ

ስልክ፡- +251-11-470-8470
ፋክስ፡- +251-11-442-0434

የሰው ሀብት፣ የግዥና ንብረት እንዲሁም የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ መረጃዎች ቢያስፈልግዎ

ኮርፖሬት የሀብት አመራር ዘርፍ

Tel: +251-11-442-1213
Fax: +251-11-442-2314

ፋይናንስ ነክ መረጃዎች ቢያስፈልግዎ

ኮርፖሬት ፋይናንስ ዘርፍ

Tel: +251-11-470-9093

ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

Downloads

“`

About EABC

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (EABC) – Company Profile

Establishment of EABC

The Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (EABC) was established in December 2015 as a federal government public enterprise under Council of Ministers Regulation No. 368/2015, with an authorized capital of 2.44 billion birr.

The Corporation, governed by the Public Enterprises Proclamation No.1314/2012, was formed through the merger of five-state owned Enterprises; namely Ethiopian Seed Enterprise, Agricultural Inputs Supply Enterprise, Agricultural Equipment and Technical Services Share Company, Agricultural Mechanization Service Enterprise, and Natural Gum Processing and Marketing Enterprises.

Currently, the Corporation, which has several branch offices and six improved seed multiplication farms for various crops in different regions, is accountable to Ethiopian Investment Holdings and is also governed by a board of directors that supervises and controls the operations and business of the EABC as well.

At present, EABC is playing its part in the implementation of the 10- year master plan for the agricultural sector at a national level. Based on this, it carries out agricultural activities ranging from land preparation to warehouse by providing integrated services through a single window, including agricultural inputs and mechanization services.

In this regard, the Corporation supplies: Improved Seeds, Solid and Liquid Fertilizers, Agrochemicals and Veterinary Drugs to customers at affordable prices.

And also, the Corporation is striving to achieve its mission by rendering the following services: Agricultural Machineries with Original Spare Parts and Implements, Construction Equipment, Chemical and Fertilizer Spraying Machines, Land development, Agricultural Mechanization, Seed Cleaning, Repair Services for Agricultural and Construction Equipment, Rental Services for Agricultural Machinery and Transport Vehicles (heavy goods transportation), Maintenance, Consulting, Technical/Vocational Training at the head office and its branches, along with after-sales services.

Additionally, Assembling Agricultural Equipment is also listed among the Corporation’s duties and responsibilities.

Furthermore, EABC is mandated to harvest, purchase, add value to, and process natural gum (GUM Arabic), as well as produce other forest products such as Gum Olibanum, Gum Myrrh & Gum Opoponax, supplying them to both domestic and international markets.

Since its establishment, the Corporation has achieved remarkable success in the agricultural sector. Building on these promising results, EABC has continued to play a vital role in modernizing agriculture, boosting production and productivity.

As a testament to its progress, the Corporation successfully met its authorized capital within a five-year period and a significant milestone that highlights its achievements in recent years. Its capital has now reached 7.564 billion birr.

Overall, the Corporation is making significant contributions to modernizing agricultural practices and enhancing productivity through integrated agricultural development activities, from land preparation to warehouse.

And also by implementing the ISO 9001:2015 quality management system, the Corporation has achieved significant and encouraging results.

Purposes of establishment

The purposes for which the Corporation is established are:

  1. to buy from domestic and international markets and supply agricultural inputs; undertake agricultural inputs market price stabilization activities;
  2. to render agricultural mechanization services, agricultural and construction equipment repair services and provide rental services of agricultural machineries and transport vehicles;
  3. to buy from domestic and international markets and supply agricultural machineries and spare parts, construction equipment and agro-chemicals;
  4. to provide necessary education for the promotion of the use of modern agricultural machineries; provide consultancy service in handling and use of agricultural machineries and provide on the job technical trainings;
  5. to harvest, buy, value add to and process natural gum, produce other forest products, and supply to domestic and international markets;
  6. to undertake agricultural land development studies and preparation of designs, agricultural land surveying, clearing, leveling, drainage and irrigation activities as well as other activities related to agricultural land development;
  7. to cause undertaking of feasibility studies, design preparation, technology selection and negotiation, erection and commissioning of new and expansion projects as well as for research activities;
  8. to cause the local designing and manufacturing of agricultural machineries and spare parts in partnership with capable local and foreign companies;
  9. to work in cooperation with the concerned educational research and training institutions in producing trained manpower in such fields, numbers and quality as required by the sector;
  10. to undertake studies, based on direction given to it by the Ethiopian Investment Holdings, for the acquisition of financial, technological and modern governance inputs (including attracting investments or participating in investments) that can help it to become competitive, both locally and globally, and profitable and implement same upon approval;
  11. to multiply, clean and process pre-basic, basic and certified seeds of various crops, vegetables and fruits; where necessary import pre-basic seeds and cause their production or sale them; to sell byproducts;
  12. to undertake research and implement improvements with respect to the supply of agricultural inputs, agricultural machineries repair, the production and marketing of natural gum, mechanization services and related matters and thereby ensure its competitiveness;
  13. to sell bonds, collateralize, negotiate and sign loan agreements with local and foreign sources in accordance with directives issued by the Ministry of Finance and on the basis of the guidance of Ethiopian Investment Holdings;
  14. to engage in other related activities for the attainment of its purposes.

EABC’s mission, vision & values

Mission

Provide agricultural inputs and technologies that can significantly improve production and productivity, enhance modern farms and agro-industries at very competitive price to accelerate the nation’s economic development.

Vision

By providing integrated agricultural inputs and mechanization service, to become a strong competitor in Africa by 2030.

Values

  • Loyalty
  • Transparency
  • Sincerity
  • Commitment
  • Mutual benefit
  • Social responsibility

The products and services of EABC

Products

Improved seeds: EABC multiplies and supplies 22 crop species and 90 varieties to farmers, semi-pastoralists, investors and institutions.

Forest products: The Corporation offers forest products, including natural gum (GUM Arabic), Gum Olibanum, Gum Myrrh & Gum Opoponax for both local and international markets.

Fertilizers: EABC imports and distributes solid and liquid (including foliar) fertilizers to customers.

Agrochemicals and Chemical spraying equipment: The Corporation supplies herbicides, pesticides, fungicides, disinfectants and chemical spraying equipment.

Agricultural equipment, construction machinery and spare parts: The Company provides reliable and modern agricultural machinery and spare parts such as tractors, combine harvesters, furrowers, disc plows, tyres, inner tubes, batteries, filters, copper wires etc. It also offers construction machinery.

Services

Integrated Agricultural Mechanization Land Development

– Seed Cleaning

– Maintenance Services for Farm  Equipment, Trucks, Vehicles, and more

– Sales and Rental Services for Farm Equipment and Construction Machinery

– Heavy  Goods  Transport  Rental  Services

– Consultancy, Technical Training and Maintenance services to its customers along with after-sales services.

Human resource

1,635

The corporation currently employs a total of 1,635 staff members, comprising 1,363 permanent employees and 272 are contract workers.

Organizational Structure

EABC is mainly organized into four sectors:

  1. Agricultural Input Product and Supply Main Sector
  2. Agricultural Machineries and Products Supply Main Sector
  3. Resource Management Sector
  4. Chief Financial Office

These sectors are accountable to the Chief Executive Officer of the Corporation. Additionally, the structure includes five business units at the head office as well as several branch offices and stations located in various regions of the country, all operating under the main sectors.

There are also 14 support units with distinct functions within the organization.

The Address of EABC’s Head Office, along with its Main Sectors and Business Units

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

City: Addis Ababa

Sub city: Akaki Kality

District/Wereda: 06 – (Saris area)

Street: On the main road to Kality adjacent to Equatorial Business Group P.L.C or FAFFA Food S.C

Tel: 0114 424177/84

P.O.BOX: 6898

Email፡ info@ethioagri.com or ethioagribusco@gmail.com

Website: www.ethioagri.com

Facebook: Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Corporate Communication and Social Responsibility Department

Tel: +251-114 42 41 25

Fax: +251-114 42 13 12

Agricultural Inputs Product and Supply Main Sector

Tel: +251-11-440-3610

Fax: +251-11-442-3613

For various improved seeds and seed cleaning service, please contact

Seeds Supply Sector

Tel: +251-11-661-2266

Fax: +251-11- 618- 6123

If you need solid & liquid (including foliar) fertilizers, agrochemicals, chemical spraying equipment and veterinary drug, please contact

Agricultural Inputs Supply Sector

Tel: +251-11-442-5623/28

Fax: +251-11-442-5622

Agricultural Machineries and Products Supply Main Sector

Tel: +251 114 42 50 12

If you are looking for farm equipment, construction machineries, spare parts, and technical training, please contact

Agricultural Equipment Supply Sector

Tel: +251-11-442-3438

Fax: +251-11-442-0895

If you are seeking integrated mechanization service and incense, myrrh and gum, please contact

Agricultural Products Sales and Mechanization Service Sector

Tel: +251 114 42 50 12

If you need rental services for transporting goods and farm equipment as well as vehicle maintenance, please contact

Trucks Administration and Maintenance Sector

Tel: +251-11-470-8470

Fax: +251-11-442-0434

If you need services related to human resources, procurement, property, as well as information and technology, please contact

Corporate Resource Management Sector

Tel: +251-11-442-1213

Fax: +251-11-442-2314  

Modernizing agriculture is our goal!

Documents

የኮርፖሬሽኑ የሀዋሳ ቅርንጫፍ ዘር እያባዛ ነው

ማስታወቂያ

የኮርፖሬሽኑ አመራሮች በአለታ ወንዶ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ