አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአርዳይታ የምርጥ ዘር ማባዣ እርሻ ልማት 3081 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፈነ።
የአርዳይታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ አዲስ ጋረዶ እንደገለጹት፣ ለ2018/2019 የምርት ዘመን መሬቱን በዘር የመሸፈን ሥራ ሰኔ 9 ቀን ተጀምሮ ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠናቋል።
አሁን ላይ በአርዳይታ የምርጥ ዘር ማባዣ እርሻ ልማት 2 ሺህ 541 ሄክታር በስንዴ፣ 525 ሄክታር በጎመን ዘር እና 15 ሄክታር በገብስ የተሸፈነ ሲሆን፣ የዘር ሽፋን ሥራው በሦስት የዘር ደረጃዎችና በ17 ዝርያዎች ተከናውኗል።
በኮርፖሬሽኑ የሚተዳደረው የአርዳይታ የምርጥ ዘር ማባዣ እርሻ ልማት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ ይገኛል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

