
ቢሾፍቱ፣ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ ተሻሽሎ በቀረበው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም በአዲስ መልክ በተዘጋጀው የኮርፖሬሽኑ ፍኖተ ካርታና የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ተሰጠ።
ማብራሪያው የተሰጠው ሰነዶቹን ባዘጋጀው የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የጥናት ቡድን ነው።
በኮርፖሬሽኑ ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም በስትራቴጂክ ፍኖተ ካርታና ዕቅድ ዙሪያ ሰሞኑን በተካሄደ ውይይት ላይ በተቋሙ የሥራ አመራር የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ለኢንስቲትዩቱ አጥኚዎች ቀርበው ምላሽ አግኝተዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የአግሪካልቸርና አግሮፕሮሰሲንግ ፖርትፎሊዮ ዳይሬክተር አቶ ባንተላይ ስንታየሁ ተገኝተው ሀሳብ ሰጥተዋል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!


