የአርሶና አርብቶ አደሩ አለኝታ የሆነው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግብርናን በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን የአንድ መስኮት የተቀናጀ አገልግሎት በጊዜ፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በመስጠት ላይ ይገኛል።
በዚህ ረገድ በተቀናጀ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ከመሬት ዝግጅት እስከ ጎተራ የሚዘልቁ የግብርና ሥራዎችን በማከናወን ላይ ነው፡፡
በተጨማሪም ለግብርና መዘመንና ለምርታማነት እድገት የላቀ አስተዋጽዖ ያላቸውን የግብርና ግብዓቶች:-
– ምርጥ ዘር፣
– ጠጣርና ፈሳሽ ማዳበሪያዎች፣
– አግሮኬሚካሎች፣
– የእንስሳት መድኃኒት እንዲሁም የእርሻ መሣሪያዎችን ከእነተቀጽላቸውና መለዋወጫቸው ለተጠቃሚዎች ያቀርባል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለደንበኞቹ እየሰጠ የሚገኘውን የአንድ መስኮት አገልግሎት የተሟላ ለማድረግ ከእርሻ መሣሪያዎች ሽያጭ በኋላ የቴክኒክና ሞያ ሥልጠና፣ የጥገናና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል።
የዘር ብጠራና የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎቶችንም ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን፥ ሁሉ ሙሉ፣ ሁሌም ዝግጁ ወደ ሆነው ኮርፖሬሽናችን ጎራ ሲሉ እንደምንጊዜውም ተደስተው ይመለሳሉ።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!





