ሀዋሳ፣ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የጀመራቸውን የለውጥ ሥራዎች ለማስቀጠል አጋዥ የሆነ ሥልጠናና የመስክ ጉብኝት ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ተደረገ።
የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙበት የመስክ ጉብኝት የተካሄደው በሀዋሳ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ “የመርሲ የቤተሰብ ዲያሪ ፋርም” ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዲያሪ ፋርሙ ባለቤት ኢያሱ ነጆ (ዶ/ር)፣ ለኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች “Transformational leader ship” በሚል ርዕስ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ የማነቃቂያ ሥልጠና /Motivational training/ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ለለውጥ ተሞክሮ ታስበው በተዘጋጁት ሥልጠናና ጉብኝት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!






