ሀዋሳ፣ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2018 በጀት ዓመት የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ተገመገመ።
የኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር፣ የቅርንጫፍና ጣቢያ ሥራ አስኪያጆች እንዲሁም የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር በተገኙበት የተገመገመው አፈጻጸም ከገቢና ትርፍ አኳያ ከዕቅድ በላይ መሆኑ ተገልጿል።
ለውጤቱ መገኘት ባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ የለውጥ ሥራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን የቀረበው የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያመለክታል።
የግምገማ መድረኩን የመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ ለውጤቱ መገኘት የኮርፖሬሽኑን የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች አመስግነው፣ በዕቅድ የተያዙ ቀሪ ሥራዎችን በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ርብርብ እንዲደረግ አሳስበዋል።
አክለውም የኮርፖሬሽኑን ዓላማና ግብ ለማሳካት የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መልእክት አስተላልፈዋል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!


