የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
  • Home
  • About Us
    • ስለ እኛ
    • About EABC
    • Board of Directors
    • Executive Management
    • Our Mission and Vision
    • Branch Offices
    • Headquarters Location
    • Organizational Structure
  • Products and Services
    • Agricultural Inputs
    • Seeds Products Supply
    • Forest Products Supply
    • Agriculture Equipment and Spare Part Supply
    • Agricultural Mechanization
    • Machinery & Heavy Duty Vehicles
  • Opportunities
    • Bids
  • Media & Publications
    • News
    • Accolades
    • Publications
    • Videos
  • Contact Us

የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ በግብርና ግብዓት፣ በእርሻ መሣሪያዎችና በግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሄደ።

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግሪን አግሮ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ – ‘ለእርሻ’ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የገበያ ትስስር መድረክ ላይ የባለድርሻ አካላት ተወያይተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በጋራ በመሥራት አነስተኛ የእርሻ መሬት ያላቸውን አርሶ አደሮች ምርታማ ማድረግ በሚቻልበት አማራጭ ዙሪያ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ደሳለኝ በላቸው እንደተናገሩት፣ መድረኩ የባለድርሻ አካላትን በማጣመር፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ ግብርናን በማዘመንና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል።

የ’ለእርሻ’ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም እንድርያስ በበኩላቸው፣ ተቋማቸው በግብርናው መስክ ሰፊ አቅምና ልምድ ካለው ከኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በመሥራቱ አነስተኛ ማሳ ያላቸውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚያስችለው አስታውቀዋል፡፡

በተመሳሳይ በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የንብ ኢንተርናሽናል፣ የዳሸን እና የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንኮች ተወካዮች ለአርሶ አደሮች የተለያዩ የብድር አማራጮችን እያቀረቡ እንደሚገኙ አስታውቀው፣ የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኩል በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከመድረኩ ከፍተኛ ግንዛቤ ማግኘታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ የግብርና ግብዓት አቅራቢዎችና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ሰጪዎች በበኩላቸው ከኮርፖሬሽኑ እና ከ’ለእርሻ’ ጋር ተባብረው ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ከውይይት መድረኩ አስቀድሞ ተሳታፊዎች በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ የእርሻ መሣሪያዎችን እና ወርክ ሾፕ ጎብኝተዋል።

በግሪን አግሮ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የተቋቋመ የዲጂታል መድረክ (Platform) የሆነው ‘ለእርሻ’፣ ዘመናዊ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አነስተኛ አርሶ አደሮችን ከግብርና ግብዓት አቅራቢዎች፣ ከግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ሰጪዎች፣ ከፋይናንስ ተቋማትና ከገበያ ጋር ከማስተሳሰር ባሻገር በአየር ንብረት ዙሪያ የምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና ‘ለእርሻ’ አነስተኛ ማሳ ያላቸውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

Twitter Facebook LinkedIn
Follow Us on Facebook

© 2025 Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Designed and Developed by the ICT department of EABC