የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
በስትራቴጂክ አጋርነት በኮንትራት ምርጥ ዘር እና የምግብ እህል የማምረት ሥራ ለመስራት የቀረበ የቅድመ ብቃት ምዝገባ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በእርሻ ሥራ ላይ ከተሰማሩ የግል ድርጅቶች፣ የሽርክና ማህበራት፣ በመንግስት ባለቤትነት የተያዙ እርሻዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎችና የግብርና ማሰልጠኛ ተቋማት፣ ማህበራት፣ ዩኒየኖች እና በክላስተር ከተደራጁ አርሶ አደሮች ጋር በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1070/2017 መሰረት በስትራቴጂክ አጋርነት የግዥ ስልት በፕሪሚየም የዋጋ ፖሊሲ ኮንትራት ዘር ብዜት እና የምግብ እህል አቅርቦት ለማምረትና ማቅረብ የሚፈልጉ ድርጅቶችን በቅድመ ብቃት መመዘኛ ለማወዳደርና ለመምረጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በእርሻ ዘርፍ የተሰማራችሁና በኮንትራት ውል ምርጥ ዘር ለማባዛትና የምግብ እህል በጥራት ለማስረከብ ፍላጎት ያላችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ያላችሁን፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የመንግስትን ግዴታዎች የተወጣ ማስረጃ፤
- የኢንቨስትመንት ፍቃድና የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ወይም በፍትህ የፀደቀ የኪራይ ውል፤
- በገቢዎች የታዘዘና ህጋዊ የምርት ርክክብ መፈጸሚያና የፋይናንስ ሰነዶች ያሟላ፤
- የአርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ማህበር ወይን ዩኒየን ከሆነ ህጋዊ ሰውነትና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
- የሥራ ፕሮፋይል፣ የባለሙያና የእርሻ ፋሲሊቲዎች እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ በኮርፖሬሽኑ ጽ/ቤት ወይም በሚቀርባችሁ የኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች (አሰላ፣ ኮፈሌ፣ ሀዋሳ፣ ባህር ዳር፣ ነቀምት፣ መቐለ፣ ቦንጋ፣ አሶሳ፣ ቻግኒ፣ አርዳይታ፣ ጊቤ፣ ወዘተ) ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
እያንዳንዱ ድርጅት ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው የቅድመ ብቃት መመዘኛ መስፈርት መሠረት (በግልጽ ማስወቂያ ሠሌዳ ላይ ይለጠፋል) የሚገመገም ሲሆን የማለፊያ መስፈርቱን የሚሟሉ ብቻ ይመረጣሉ፡፡
እያንዳንዱ ድርጅት ኮርፖሬሽኑ ባዘጋጀው የቅድመ ብቃት መመዘኛ መስፈርት መሠረት (በግልጽ ማስወቂያ ሠሌዳ ላይ ይለጠፋል) የሚገመገም ሲሆን የማለፊያ መስፈርቱን የሚሟሉ ብቻ ይመረጣሉ፡፡
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
ለበለጠ መረጃ፡-
📞 0992035347 / 0920393512 / 0911560223
📮 ፖ.ሳ.ቁ: 6898
📍 አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 06 (ሳሪስ አካባቢ፤ ከፋፋ ምግብ አ/ማ ጀርባ)
🌐 Website: https://www.ethioagri.com
📞 0992035347 / 0920393512 / 0911560223
📮 ፖ.ሳ.ቁ: 6898
📍 አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 06 (ሳሪስ አካባቢ፤ ከፋፋ ምግብ አ/ማ ጀርባ)
🌐 Website: https://www.ethioagri.com