
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግብርናው ዘርፍ ከቤላሩስ ኩባንያዎች ጋር በሽርክና ለመሥራት በሚችልባቸው መስኮች ዙሪያ ከሀገሪቱ የልዑካን ቡድን ጋር ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ተወያየ።
ምክክሩ የቤላሩስ ኩባንያዎች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በሽርክና በመሥራት ዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎችን ገጣጥመው ለአርሶ አደሩና ለልማት ድርጅቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ በኮርፖሬሽኑ በኩል የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ እና የእርሻ መሣሪያዎችና የግብርና ውጤቶች አቅርቦት ዐቢይ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተከስተ ክፍሌ (ዶ/ር) እንዲሁም የቤላሩስ የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ አመራር፣ በኬንያ የቤላሩስ አምባሳደርና በኢትዮጵያ የቤላሩስ ቆንስላ ጽ/ቤት ኃላፊ ተሳትፈዋል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!
