የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
  • Home
  • About Us
    • ስለ እኛ
    • About EABC
    • Board of Directors
    • Executive Management
    • Our Mission and Vision
    • Branch Offices
    • Headquarters Location
    • Organizational Structure
  • Products and Services
    • Agricultural Inputs
    • Seeds Products Supply
    • Forest Products Supply
    • Agriculture Equipment and Spare Part Supply
    • Agricultural Mechanization
    • Machinery & Heavy Duty Vehicles
  • Opportunities
    • Bids
  • Media & Publications
    • News
    • Accolades
    • Publications
    • Videos
  • Contact Us

ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአርሶ አደሩን አቅም ለማሳደግና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጓል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018(ኢዜአ)፦ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአርሶ አደሩን የፋይናንስ አቅም ማሻሻልና የግብርና ግብዓቶች ተጠቃሚነትን ማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሺእመቤት ነጋሽ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የግሪን አግሮ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ “ለእርሻ” በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመዋል።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሺእመቤት ነጋሽ እና የግሪን አግሮ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ “ለእርሻ” ሥራ አስፈፃሚ አብረሃም እንዲሪያስ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም አርሶ አደሮችን የፋይናንስ አቅም ለማሻሻልና የግብርና ግብዓቶች ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሺእመቤት ነጋሽ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለመጨመር እየሰራ ይገኛል።

ስምምነቱ አርሶ አደሩ የግብርና ግብዓቶችን፣ የፋይናንስ አገልግሎቶችንና የሜካናይዜሽን አማራጮችን በቀላሉ ማግኘት የሚችልበትን መንገድ ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል።

በዚህም መሰረት ብሔራዊ የግብርና ፍኖተ ካርታ እና ፋይናንስ አካታችነት ትግበራ ላይ በጋራ በመስራት እስከ 2030 ድረስ ለአንድ ሚሊየን አነስተኛ አርሶ አደሮች የብድር እድል ለማመቻቸት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Twitter Facebook LinkedIn
Follow Us on Facebook

© 2025 Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Designed and Developed by the ICT department of EABC