አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8/2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የግሪን አግሮ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ (‘ለእርሻ’) አነስተኛ ማሳ ያላቸውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡
በግብርናው ዘርፍ በጋራ ለመሥራት የሚያስችለው ይህ ስምምነት (MoU) አነስተኛ ማሳ ያላቸውን አርሶ አደሮች የፋይናንስ አቅም ለማሻሻል፣ የግብርና ግብዓቶችና የሜካናይዜሸን አገልግሎት ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በሥልጠና ለማጎልበት ያግዛል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

















