ጅማ፣ የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጽያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የበላይ አመራር ከቅርንጫፍ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በጅማ ከተማ ተወያየ።
ውይይቱ ኮርፖሬሽኑን ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ ባለፉት ሳምንታት በአዳማና ሀዋሳ ከተሞች ከተዘጋጁት መድረኮች ጋር ተመሳሳይ ነው።
በዛሬው መድረክ የጊቤ፣ የቦንጋ፣ የታማሻሎ፣ የአሶሳና የነቀምት ቅርንጫፎች የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
በዚሁ ወቅት ለውይይት መነሻ የሚሆኑ የተቋሙ የነባራዊ ሁኔታ የዳሰሳ ጥናት ውጤት፣ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም ሰነዶች በኮርፖሬት ሀብት አመራር ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደሳለኝ በላቸው ቀርበው ውይይት ተደርጓል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!



