የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
  • Home
  • About Us
    • ስለ እኛ
    • About EABC
    • Board of Directors
    • Executive Management
    • Our Mission and Vision
    • Branch Offices
    • Headquarters Location
    • Organizational Structure
  • Products and Services
    • Agricultural Inputs
    • Seeds Products Supply
    • Forest Products Supply
    • Agriculture Equipment and Spare Part Supply
    • Agricultural Mechanization
    • Machinery & Heavy Duty Vehicles
  • Opportunities
    • Bids
  • Media & Publications
    • News
    • Accolades
    • Publications
    • Videos
  • Contact Us

ኮርፖሬሽኑ እና የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በጋራ ለመሥራት ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ):-የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በምግብ እህል ምርትና አቅርቦት በጋራ ለመሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ተወያዩ።

በውይይቱ ወቅት ኮርፖሬሽኑ ኮሚሽኑ በመጠባበቂያ የሚያከማቸውንና ለዕለት ደራሽ እርዳታ የሚያሰራጨውን የምግብ እህል (ስንዴ፣ በቆሎና ሩዝ) አምርቶ እንዲያቀርብ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው 54 ሺህ ኩንታል ስንዴ በሽያጭ ለኮሚሽኑ ቀርቧል፡፡

በውይይቱ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) እና የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

Twitter Facebook LinkedIn
Follow Us on Facebook

© 2025 Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Designed and Developed by the ICT department of EABC