የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
  • Home
  • About Us
    • ስለ እኛ
    • About EABC
    • Board of Directors
    • Executive Management
    • Our Mission and Vision
    • Branch Offices
    • Headquarters Location
    • Organizational Structure
  • Products and Services
    • Agricultural Inputs
    • Seeds Products Supply
    • Forest Products Supply
    • Agriculture Equipment and Spare Part Supply
    • Agricultural Mechanization
    • Machinery & Heavy Duty Vehicles
  • Opportunities
    • Bids
  • Media & Publications
    • News
    • Accolades
    • Publications
    • Videos
  • Contact Us

የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ግብርናን በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እንደሚሠሩ ቃል ገቡ

አዳማ፣ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጽያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ግብርናን በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ቃል ገቡ።

ይህ የተገለጸው በኮርፖሬሽኑ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ዕቅድ አፈጻጸም፣ በተቋሙ የነባራዊ ሁኔታ የዳሰሳ ጥናትና በሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም ዙሪያ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በአዳማ ኃይሌ ሪዞርት በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ ላይ በሦስት ወቅታዊ የኮርፖሬሽኑ የውይይት አጀንዳዎች ላይ ገለጻ ያደረጉት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ፣ የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በጋራ ከሠሩ የሀገሪቷን የምግብ ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ ግንባር ቀደም ሚና መጫወት ይችላሉ ብለዋል።

ኮርፖሬሽኑ ካሉበት ውስብስብ ችግሮች ተላቆ በመንግሥት የተሰጠውን ተልዕኮ መወጣት እንዲችል የነባራዊ ሁኔታ የዳሰሳ ጥናት መደረጉንና በጥናቱ ምክረ ሀሳብ መነሻም ተቋሙን ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ የሚያሸጋግሩ የሪፎርም ሥራዎች መጀመራቸውን ጠቁመዋል።

አክለውም ፍኖተ ካርታ እየተዘጋጀ መሆኑንና በቀጣይ የስትራቴጂክ ዕቅድና የቢዝነስ ፕላን ሰነዶች እንደሚዘጋጁ አስታውቀዋል።

የኮርፖሬሽኑ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ የተቋሙን ዘላቂ ህልውና እና የገበያ ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ በጋራና በትኩረት መሥራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ በጥናት የተለዩ ችግሮችን ለመፍታት የተጀመረውን የሪፎርም ሥራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የአግሪካልቸርና አግሮፕሮሰሲንግ ፖርትፎሊዮ ዳይሬክተር አቶ ባንተላይ ስንታየሁ፣ ኮርፖሬሽኑ ለምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥና ለሀገር መዋለ ነዋይ እድገት ያለው ሚና ጉልህ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህ ረገድ ሆልዲንጉ በተለያዩ መስኮች ተቋሙን እንደሚደግፍ አስታውቀዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ በዳሰሳ ጥናቱ ውጤት፣ በሪፎርም ሥራዎችና በቀጣይ አቅጣጫዎች የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን፣ አመራሩና ሠራተኛው ለለውጥ ዝግጁና ቁርጠኛ መሆናቸውን ቃል ገብተዋል።

በውይይቱ ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ በሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና በሆልዲንጉ ተወካይ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶአል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

Twitter Facebook LinkedIn
Follow Us on Facebook

© 2025 Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Designed and Developed by the ICT department of EABC