አዲስ አበባ፣ ጥር 24/2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ የተቋሙን የእርሻ መሣሪያዎች አቅርቦት ጥር 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጎበኘ።
ከጉብኝቱ በኋላ የኮርፖሬሽኑን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።
የተቋሙ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ ለውይይት ቀርቧል።
ከመስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ኮርፖሬሽኑን በሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢነት፣ በምክትል ሰብሳቢነትና በአባልነት እየመሩ የሚገኙት:-
ወ/ሮ ዓለምፀሀይ ጳውሎስ – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር – የቦርድ ሰብሳቢ
አቶ አዲሱ አረጋ – የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር – የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ
ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው – በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ – የቦርድ አባል
ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ – የቦርድ አባል
አቶ አቤ ሳኖ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት – የቦርድ አባል
ታከለ ኡማ (ኢ/ር) – የኢትዮ – ጂቡቲ የምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ – የቦርድ አባል
ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) – የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር – የቦርድ አባል
አቶ ኪያ ተካልኝ – ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ – የቦርድ አባል አቶ ዳንኤል ስለሺ – በኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የተመረጡ – የቦርድ አባል ናቸው።






























