የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
  • Home
  • About Us
    • ስለ እኛ
    • About EABC
    • Board of Directors
    • Executive Management
    • Our Mission and Vision
    • Branch Offices
    • Headquarters Location
    • Organizational Structure
  • Products and Services
    • Agricultural Inputs
    • Seeds Products Supply
    • Forest Products Supply
    • Agriculture Equipment and Spare Part Supply
    • Agricultural Mechanization
    • Machinery & Heavy Duty Vehicles
  • Opportunities
    • Bids
  • Media & Publications
    • News
    • Accolades
    • Publications
    • Videos
  • Contact Us

ኮርፖሬሽኑ ለግብርና ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ተቋም መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለግብርና ትራንስፎርሜሽን እመርታ ወሳኝ ተቋም መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት  ገለጸ።

ይህ የተገለጸው የም/ቤቱ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትና በተቋሙ የአዳማ ቅርንጫፍ የግብርና ግብዓትና የእጣን መጋዘኖች ባካሄደው የመስክ ምልከታና ውይይት ላይ ነው።

በውይይቱ ወቅት ኮርፖሬሽኑ የግብርና ትራንስፎርሜሽን እመርታንና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ተቋም በመሆኑ በመንግሥት ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው ቋሚ ኮሚቴው አስታውቋል።

ኮርፖሬሽኑ በመንግሥት የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ እንዲያሳካ የተቋሙ ሥራ አመራርና ሠራተኞች በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባቸው ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ መለሰ መና በሰጡት አስተያየት፣ የኮርፖሬሽኑ አዲሱ አመራር የተቋሙን አጠቃላይ ሁኔታ በአጭር ጊዜ በመረዳት ተቋሙ በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ፣ ምርታማና አትራፊ ሆኖ እንዲቀጥል እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው፣ በዚህ ረገድ ቋሚ ኮሚቴው ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ኮርፖሬሽኑ በጥናት ላይ የተመሰረተና በቴክኖሎጂ የታገዘ የግዥና ሽያጭ አሠራር መዘርጋት እንዳለበት የጠቆሙት ሰብሳቢው፣ የግብርና ግብዓቶችን በጊዜና በጥራት ለተጠቃሚዎች በማቅረብም ዘርፉን የማዘመን ተልዕኮ ማሳካት ይጠበቅበታል ብለዋል።

አክለውም ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ በአጽንዖት ተናግረዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ ስለሺ ኮሬ (ዶ/ር ኢንጂነር) በበኩላቸው፣ የኮርፖሬሽኑ አዲሱ አመራር ለተቋሙ ለውጥ የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው፣ ለተሻለ ውጤት ከሠራተኛ ጋር በቅርበት መሥራትና ዘመናዊ አሠራርን መከተል እንደሚገባ አስረድተዋል።

በዕለቱ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ለቋሚ ኮሚቴው አቅርበዋል።

በገለጻቸው ኮርፖሬሽኑ በግብርናው ዘርፍ የካበተ ልምድ እንዳለው፣ የትልቅ ሀብት ባለቤት እንደሆነ፣ በተለያዩ የግብርና ዘርፎች መስፋትና ማደግ የሚችል ተስፋ ያለው ግዙፍ ተቋም መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴው አብራርተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በኮርፖሬሽኑ የአዳማ ቅርንጫፍ የግብርና ግብዓትና የእጣን መጋዘኖች የመስክ ምልከታ ከማድረጉ በፊት ከተቋሙ ዋና መ/ቤት የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ከተውጣጡ ሠራተኞች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቷል።

በቋሚ ኮሚቴ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
                  ###
  ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

Twitter Facebook LinkedIn
Follow Us on Facebook

© 2026 Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Powered by the ICT department of EABC