አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፡- መልካም ሥነ ምግባር የተላበሱ አመራሮችና ሠራተኞች ለተቋም ስኬት መሠረት መሆናቸውን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ገለጹ።
ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ ይህንን የገለጹት፣ ለኮርፖሬሽኑ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ከታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በዋናው መ/ቤት በተዘጋጀ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና የሥልጠና መርሐ ግብር ላይ ነው።
ወ/ሮ የሺእመቤት ሥልጠናውን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልእክት፣ የኮርፖሬሽኑ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች መልካም ሥነ ምግባርን በመላበስ፣ ሙስናን በመጸየፍና ብልሹ አሠራርን በመከላከል ኃላፊነትን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
አክለውም ኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የሀገር ሀብትና ንብረት የሚያንቀሳቅስና ለሀገሪቷ ኢኮኖሚያዊ እድገት የጀርባ አጥንት የሆነ ስትራቴጂካዊ ተቋም በመሆኑ ሕጎችን፣ መመሪያዎችንና ተገቢ አሠራሮችን ጠብቆ ሥራዎችን ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ከፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ሥልጠና፣ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የኮሚሽኑ ተባባሪ አሠልጣኝ ዘመዴ ዛኪ (ዶ/ር) አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!





