የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
  • Home
  • About Us
    • ስለ እኛ
    • About EABC
    • Board of Directors
    • Executive Management
    • Our Mission and Vision
    • Branch Offices
    • Headquarters Location
    • Organizational Structure
  • Products and Services
    • Agricultural Inputs
    • Seeds Products Supply
    • Forest Products Supply
    • Agriculture Equipment and Spare Part Supply
    • Agricultural Mechanization
    • Machinery & Heavy Duty Vehicles
  • Opportunities
    • Bids
  • Media & Publications
    • News
    • Accolades
    • Publications
    • Videos
  • Contact Us

ኮርፖሬሽኑና የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፣ ኮርፖሬሽኑ ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ አግሮ ኬሚካሎች፣ የእርሻ መሣሪያዎች እና የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሮች እና ሌሎች ተጠቃሚዎች በብዛትና በጥራት ማቅረብ የሚያስችል አቅምና ልምድ እንዳለው አስረድተዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ኮርፖሬሽኑ በመግባቢያ ሰነድና በውል በታሰረ አካሄድ ተቋማትም ሆኑ አርሶ አደሮች የሚፈልጉትን የግብርና ግብዓቶችና የእርሻ መሣሪያዎች በማምረት፣ በመገጣጠምና ከውጭ በማስመጣት ማቅረብ እንደሚችል አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ አባል ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ተቋማቸው የሀገሪቷን ግብርና ለማዘመን ተመሳሳይ ዓላማ ይዞ እየሠራ ከሚገኘው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ተቀራርቦ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

አክለውም ተቋማቸው ዘመናዊ የአመራረት ዘዴን በሀገር ደረጃ ለማስፋፋት ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች በድጋፍ መልክ እንደሚያቀርብ ጠቁመው፣ የመንግሥት ለመንግሥት ግዥ አሠራርን በመከተል ከኮርፖሬሽኑ ትራክተሮችን በመግዛት ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ በጋራ እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በቅርቡ ከኮርፖሬሽኑ ስድስት ትራክተሮችን ለትግራይ እና ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች መግዛቱን እንዲሁም በቀጣይ ተጨማሪ ትራክተሮችን ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው የኮርፖሬሽኑ የእርሻ መሣሪያዎችና የግብርና ውጤቶች አቅርቦት ዐቢይ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተከስተ ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የኮርፖሬሽኑን ምርትና አገልግሎቶች ለግብርና ሚኒስቴር እና ለሌሎች ተቋማት በስፋት ለማስተዋወቅ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከውይይቱ ቀደም ብሎ ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) እና የግብርና ሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ በቀለ በኮርፖሬሽኑ በክምችት የሚገኙ የእርሻ መሣሪያዎችን እና መለዋወጫዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

Twitter Facebook LinkedIn
Follow Us on Facebook

© 2025 Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Designed and Developed by the ICT department of EABC