የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
  • Home
  • About Us
    • ስለ እኛ
    • About EABC
    • Board of Directors
    • Executive Management
    • Our Mission and Vision
    • Branch Offices
    • Headquarters Location
    • Organizational Structure
  • Products and Services
    • Agricultural Inputs
    • Seeds Products Supply
    • Forest Products Supply
    • Agriculture Equipment and Spare Part Supply
    • Agricultural Mechanization
    • Machinery & Heavy Duty Vehicles
  • Opportunities
    • Bids
  • Media & Publications
    • News
    • Accolades
    • Publications
    • Videos
  • Contact Us

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጽሕፈት ቤታቸው ተወያዩ።

በውይይቱም የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በምርጥ ዘር አቅርቦት ለማሳደግ እንዲሁም ዘርፉን በማዘመን ረገድ እስካሁን ሲያከናውን በቆየባቸው ጉዳዮች እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ዓላማ ያደረገ ነው።

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በክልሉ ቦንጋ ከተማ የተቀናጀ የግብርና ግብዓት እና ሜካናይዜሽን ማዕከል በመገንባት ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተለያዩ ምርጥ ዘር ምርትና አቅርቦት፣የግብርና ሜካናይዜሽን (ማሽነሪ አቅርቦትና ጥገና አገልግሎት፣ ⁠የግብርና ግብዓትአርቦትና ስርጭት እና የእንስሳት ሃብት ልማት የሥጋና ወተት ምርት ማሳደግ

ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

ኮርፖሬሽኑ የጀመራቸው ሥራዎች ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገሩ የክልሉ መንግስት በአስፈላጊ ጉዳዮች በጋራና በተቀናጀ እንደሚሰራ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

ኮርፖሬሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቦንጋ ከተማ ያስገነባው የተቀናጀ የግብርና ግብዓት እና መካናይዜሽን ቀደም ሲል ይስተዋል የነበረው የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር በእጅጉ ከመቅረፍ ባሻገር ለሌሎች መትረፍ የሚችል አቅም እየፈጠረ እንደሚገኝ ነው የገለጹት።

የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር በመፍታት የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በክልሉ የምርጥ ዘር ድርጅት ተቋቁመው ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል።

በክልሉ የተገነባው የተቀናጀ የግብርና ግብዓት እና መካናይዜሽን ማዕከል በክልሉ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ችግር እየፈታ ካለው ሥራ በተጨማሪም በሌሎች በገበያ ተኮር ምርቶችን በብዛትና በጥራት ማምረት ላይ ትኩረት እንዲያደርግም ጠቁመዋል።

ኮርፖሬሽኑ በክልሉ የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ ዘመናዊ የእርሻ ማሽነሪዎች እና መካናይዜሽን አሠራር ለመከተል በሚያደርገው ጥረት የኮርፖሬሽኑ ሁሉ ዓቀፍ ድጋፍ እንዲጠናክር ጠይቀዋል።

በክልሉ ከግብርና ግብዓት አቅርቦት ለማሳደግ እንዲሁም የዘርፉን ለማዘመን በሚደረገው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከክልሉ ጋር በመቀናጀት ይሰራል ሲሉ የኮርፖረሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ የገለጹት።

ከኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከቦንጋ ማዕከል ጋር ምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር መፍታት እንዲሁም ዘርፉን ማዘመን በሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ተናግረዋል።

በፍቅር ከበደ

Twitter Facebook LinkedIn
Follow Us on Facebook

© 2025 Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Designed and Developed by the ICT department of EABC