የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
  • Home
  • About Us
    • ስለ እኛ
    • About EABC
    • Board of Directors
    • Executive Management
    • Our Mission and Vision
    • Branch Offices
    • Headquarters Location
    • Organizational Structure
  • Products and Services
    • Agricultural Inputs
    • Seeds Products Supply
    • Forest Products Supply
    • Agriculture Equipment and Spare Part Supply
    • Agricultural Mechanization
    • Machinery & Heavy Duty Vehicles
  • Opportunities
    • Bids
  • Media & Publications
    • News
    • Accolades
    • Publications
    • Videos
  • Contact Us

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከተቋሙ የሥራ አመራር  ጋር ተዋወቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20/2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከተቋሙ የሥራ አመራር ጋር ትውውቅ አደረጉ።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ መስከረም 20/2018 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ተገኝተው ከሥራ አመራሩ ጋር ተዋውቀዋል።

በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፣ ኮርፖሬሽኑ ግብርናን በማዘመንና የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት እንደተጣለበት አስታውቀው፣ በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩና አዳዲስ የልማት ሥራዎችን በጋራ ጥረት ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ይህንን ለመፈጸም ኮርፖሬሽኑ በሰው ኃይል፣  በአደረጃጀት፣ በአሠራርና በሀብት የተሟላ እንደሆነ መረዳታቸውን ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ነገ ረቡዕ መስከረም 21/2018 ዓ.ም የኮርፖሬሽኑን ሠራተኞች እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል።

በተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ቦታዎች ሀገራቸውን ያገለገሉት ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ ከመስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተመድበዋል።
                            ###
           ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!

Twitter Facebook LinkedIn
Follow Us on Facebook

© 2025 Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Designed and Developed by the ICT department of EABC