የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation
  • Home
  • About Us
    • ስለ እኛ
    • About EABC
    • Board of Directors
    • Executive Management
    • Our Mission and Vision
    • Branch Offices
    • Headquarters Location
    • Organizational Structure
  • Products and Services
    • Agricultural Inputs
    • Seeds Products Supply
    • Forest Products Supply
    • Agriculture Equipment and Spare Part Supply
    • Agricultural Mechanization
    • Machinery & Heavy Duty Vehicles
  • Opportunities
    • Bids
  • Media & Publications
    • News
    • Accolades
    • Publications
    • Videos
  • Contact Us

ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተመደቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20/2018 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ ከመስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲሠሩ መድቧል፡፡


የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትን (ኢኢግልድ) ከሚያዝያ 2012 ዓ.ም እስከ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ከአምስት ዓመታት በላይ ያስተዳደሩት ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ፣ ከመስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተመድበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባል የሆኑት ወይዘሮ የሺእመቤት፣ ከመስከረም 2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 2013 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ጊዜያት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነበሩ፡፡

በ11 ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቆይታቸው የንግድና ኢንደስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የንዑስና ዋና ኮሚቴ ሰብሳቢ፤  የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነት ቦታዎች ሀገራቸውን ያገለገሉት ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ አስተዳደርና ፖሊሲ ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪ አላቸው፡፡ 

Twitter Facebook LinkedIn
Follow Us on Facebook

© 2025 Ethiopian Agricultural Businesses Corporation

Designed and Developed by the ICT department of EABC