የኮርፖሬሽኑ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑን የተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች መሆኑን የተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ ገለጸ።
ቦርዱ ይህን የገለጸው፣ በግብርና ሚኒስቴር የስብሰባ አዳራሽ ሚያዝያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም የኮርፖሬሽኑ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ነው።በዚሁ ወቅት የግብርና ሚኒስትር እና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ ተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት የገቢና ትርፍ ዕቅዱን በቀሪዎቹ ሁለት ወራት እንዲያሳካ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም በበኩላቸው፣ ኮርፖሬሽኑ እንደ ባለፉት ዓመታት የዘንድሮውን በጀት ዓመት የገቢና የትርፍ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ እንደሚያሳካ ተናግረዋል። ዕቅዱን ለማሳካትም የኮርፖሬሽኑ የዋና መ/ቤት የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከመደበኛ ሥራቸው በተጨማሪ በወር ሁለት ቅዳሜ ቀናትን በሥራ ለማሳለፍ ተስማምተው ደንበኞችን በማገልገል ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
በተመሳሳይ በተቋሙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የቅዳሜ ሥራ መደበኛ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ክፍሌ፣ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ቀሪ የኦፕሬሽን ሥራዎችን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመምራት፣ ገቢን በመጨመርና ወጪን በመቀነስ የኮርፖሬሽኑን ዕቅድ ማሳካት ይቻላል ብለዋል።
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!




