ለኢትዮጵያ የግብርና ልማት ተስማሚ የሆኑ የእርሻ መሣሪያዎች እና የግብርና ግብዓቶች – ከኢግሥኮ
ሁሌም ሙሉ፣ ዘወትርም ዝግጁ ሆኖ ወደሚጠብቅዎ የአርሶና አርብቶ አደሩ አለኝታ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) ጎራ ይበሉና ለእርስዎ የንግድና የልማት ሥራዎች ይስማማሉ ብለን ያቀረብናቸውን ትራክተሮች፣ ኮምባይን ሀርቨስተሮች፣ ማረሻዎች፣ መከስከሻዎች፣ መስመር ማውጫዎች፣ ኬሚካል መርጫ ማሽኖች፣ የእርሻና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች መለዋወጫዎች፣ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ፊልትሮዎች፣ አግሮኬሚካሎች፣ ፈሳሽ ማዳበሪያዎች ወዘተ በተመጣጣኝ ዋጋ ገዝተው ያትርፉ።
ሁሌም በእናንተ ውድ ደንበኞቻችን ጥያቄና ፍላጎት ከታወቁ የውጭ ኩባንያዎች በምናስመጣቸው የእርሻና የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች፣ አግሮኬሚካሎች፣ የእንስሳት መድኃኒቶች፣ ፈሳሽ ማዳበሪያዎችና መለዋወጫዎች፤ በምናቀርበው ምርጥ ዘር እንዲሁም በምንሰጠው የአንድ መስኮት አገልግሎት ቀዳሚ ተመራጭ ተቋም አድርጋችሁ ስለመረጣችሁን የላቀ ደስታና ኩራት እንደሚሰማን በዚህ አጋጣሚ በአክብርዎት ለመግለጽ እንወዳለን።
ለበለጠ መረጃ:- 0911 157091፣ 0911 223675
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!


























