ክቡራን ደንበኞቻችን፣
የአርሶና አርብቶ አደሩ አለኝታ የሆነው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ከሰኞ እስከ አርብ ከሚሰጠው መደበኛ አገልግሎት በተጨማሪ ከነገ ቅዳሜ መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወር ሁለት ቅዳሜ ቀናትን ቢሮዎቹን ክፍት በማድረግ ሊያገለግላችሁ መዘጋጀቱን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።
በዚህ መሰረት:- መጋቢት 6፣ መጋቢት 20፣ ሚያዝያ 4፣ ሚያዝያ 18፣ ግንቦት 2፣ ግንቦት 16፣ ሰኔ 7 እና ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት ከ2:00 – 6:00፤ ከሰዓት በኋላ ከ7:00 – 11:00 ድረስ ቢሮዎቻችን ክፍት ሆነው ይጠብቋችኋል።
ማስታወሻ
በቅርንጫፎቻችን ዘወትር ቅዳሜ ለደንበኞች የምንሰጠው አገልግሎት እንደተለመደው ይቀጥላል።
ይምጡ! በአገልግሎታችን ተደስተው ይመለሳሉ።
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን