ማስታወቂያ
ክቡራን ደንበኞቻችን፣
የአርሶና አርብቶ አደሩ አለኝታ የሆነው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ከሰኞ እስከ አርብ ከሚሰጠው መደበኛ አገልግሎት በተጨማሪ ከነገ ቅዳሜ መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወር ሁለት ቅዳሜ ቀናትን ቢሮዎቹን ክፍት በማድረግ ሊያገለግላችሁ መዘጋጀቱን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።
በዚህ መሰረት:- መጋቢት 6፣ መጋቢት 20፣ ሚያዝያ 4፣ ሚያዝያ 18፣ ግንቦት 2፣ ግንቦት 16፣ ሰኔ 7 እና ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት ከ2:00 – 6:00፤ ከሰዓት በኋላ ከ7:00 – 11:00 ድረስ ቢሮዎቻችን ክፍት ሆነው ይጠብቋችኋል።
ማስታወሻ
በቅርንጫፎቻችን ዘወትር ቅዳሜ ለደንበኞች የምንሰጠው አገልግሎት እንደተለመደው ይቀጥላል።
ይምጡ! በአገልግሎታችን ተደስተው ይመለሳሉ።
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ለክቡራን ደንበኞቻችን የቀረቡ የአውሮፓ ስሪት የኬሚካል መርጫ መሣሪያዎች
ከአውሮፓ በአስመጣቸው ‘ዱዝ-ፋር’ እና ‘ዜቶር’ ትራክተሮች በደንበኞቹ ዘንድ ምስጋና እና አድናቆት የተቸረው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ)፣ እነሆ የገበያውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በትራክተር የሚጎተቱ 3 ሺህ ሊትር አግሮኬሚካል የመያዝ አቅም ያላቸውን ጣልያን ሰራሽ ማሽኖች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረቡን ሲገልጽ፣ ጥራት ላይ በመተማመን ነው። የጣልያኑ ሶጅማ ኩባንያ ምርት የሆኑት እነዚህ የኬሚካል መርጫ መሣሪያዎች 24 ሜትር ስፋት ያላቸው ሲሆን፣ ቁመታቸው እስከ 2 ሜትር ድረስ ከፍ ይላል። እርስዎ ቀድመው ይምጡና ይውሰዱ፤ እኛ ደግሞ ማገልገሉን እናውቅበታለን።
አድራሻ:- ወደ ቃሊቲ በሚወስደው ዋና መንገድ ከኢኳቴሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ወይም ከፋፋ ምግብ አክስዮን ማኅበር 200 ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114 – 423 438 ወይም 0911 157 091 ላይ ይደውሉ።






ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው! የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የቼክ ሪፐብሊክ ‘ዜቶር (ZETOR)’ ትራክተሮች ዛሬም በገበያ ላይ ናቸው

ከጣልያኑ ዱዝ-ፋር ትራክተር በተጨማሪ 110፣ 120 እና 136 የፈረስ ጉልበት ያላቸውን ‘ዜቶር’ በመባል የሚታወቁ የቼክ ሪፐብሊክ ታዋቂ ትራክተሮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል።ይሄም ብቻ አይደለም፤ ወደ ተቋማችን ጎራ ሲሉ ሌሎች ትርፋማ የሚያደርግዎትን ማረሻ፣ መከስከሻ፣ መስመር ዋውጫ፣ ኬሚካል መርጫ፣ ዘር መዝሪያ፣ ማዳበሪያ መበተኛ፣ የእርሻ መሣሪያዎችና የከባድ ተሽከርካሪዎች ጎማ፣ ባትሪ እና ፊልትሮ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በጥራትና በብዛት ያገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ :- 0911 157091 ወይም 0114 – 42 34 38 ላይ ይደውሉ።










ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ዉግዛል/WUXALማክሮሚክስ ፈሳሽ ማዳበሪያ – በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮች እና ባለሃብቶች ምርጫ
በዋና መ/ቤት እና በክልሎች ባሉት 25 ቅርንጫፎች ለአርሶ አደሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮች እና ባለሃብቶች እያከፋፈለ የሚገኘው ዉግዛል/WUXALማክሮሚክስ ፈሳሽ ማዳበሪያ በሰብል፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ቅጠል ላይ የሚረጭ ነው።ዉግዛል/WUXAL የምርት ጥራት እና ምርታማነት እንዲጨምር ከማገዙ ባሻገር የሰብሎች በሽታን የመቋቋም አቅም እንዲያድግ ያስችላል፡፡ ምን ይሄ ብቻ፤ ምርትን በአጭር ጊዜ፣ በከፍተኛ መጠንና ጥራት ለማምረት እንዲሁም የአፈር ብክለትና የማዳበሪያ ንጥረ ነገር ትነት መጠንን ለመቀነስም ይጠቅማል።አግሉኮን በተባለ የጀርመን ኩባንያ የሚመረተው ይህ ማዳበሪያ በዓለም ገበያ የተዋወቀው እ.ኤ.አ በ1963 ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ75 ሀገራት ተደራሽ ሆኗል።
ይምጡ! ይዘዙን! ያትርፉ!
ለበለጠ መረጃ:- 0911 223 675 ወይም 0919 748 792 ላይ ይደውሉ።
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!