አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20/2017 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን ኮካ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተረከበውን 5 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት የሚያስችለውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራ ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀመረ።
በልማት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ የምዕራብ ኦሞ ዞን፣ የማጂና ሱሪ ወረዳዎች አመራሮች እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ ተወካይ ተገኝተዋል።
ኮርፖሬሽኑ ኮካ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በተረከበው መሬት ምርጥ ዘር እንደሚያባዛ እና ወደ ውጭ የሚላኩ ሰብሎችን እንደሚያመርት መገለጹ ይታወሳል።
ሦስተኛ የልማት መዳረሻው ከሆነው የኮካ እርሻ መሬት ልማት በተጨማሪ በክልሉ የታማሻሎ የምርጥ ዘር ማባዣ እርሻ ልማት እና በቅርቡ እንደሚመረቅ የሚጠበቀውን የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓት እና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ፕሮጀክት እያስተዳደረ ይገኛል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!