* “ተቋሙ ወደ ምዕራብ ኦሞ ዞን ይዞት የመጣው ዕድል አምልጦን ትውልድ እንዳይወቅሰን መጠንቀቅ አለብን”
የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ
* “መከላከያ ሠራዊት ከክልሉ የፀጥታ ኃይል እና ከማኅበረሰቡ ጋር በመሆን ለአካባቢው ዘላቂ ሰላም እና ልማት በጋራ እየሰራ ይገኛል።” ጄነራል አስራት ዴኔሮ
* “እስከዛሬ ሳናውቅ በልማት ወደ ኋላ በመቅረታችን ተጎድተናል፤ አሁን ግን ኮርፖሬሽኑ ይዞ የመጣው የልማት ዕድል ሊያመልጠን አይገባም።” የምዕራብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች
ማጂ ወረዳ – ቱም፣ ህዳር 26/2017 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሦስተኛ የልማት መዳረሻው የሆነውን የኮካ እርሻ መሬት ልማት ለመጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ።
ተቋሙ ይህን የአስታወቀው በምዕራብ ኦሞ ዞን ኮካ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ ከክልሉ በተረከበው 5 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ምርጥ ዘር የማባዛት እና ወደ ውጭ የሚላኩ ሰብሎችን የማምረት ሥራ ለመጀመር ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በማጂ ወረዳ ቱም ከተማ በተካሄደ የውይይት መድረክ ነው።የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም እንደተናገሩት፣ ኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ግብርናን የማዘመን ተልዕኮ በማንገብ በሀገር ደረጃ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ፈርጀ-ብዙ ርብርብ ውስጥ የድርሻውን ለማበርከት በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡የዚህ እንቅስቃሴ አንዱ የልማት መዳረሻ ደግሞ የሰብል ዘር እና የወጪ ሰብሎችን ለማምረት በኮርፖሬሽኑ የተመረጠው የኮካ አካባቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልን ለግብርና ልማት ሲመርጥ በምክንያት መሆኑን አብራርተዋል፡፡በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መቱ አኩ፣ በአስተላለፉት መልእክት፣ “ተቋሙ ወደ ምዕራብ ኦሞ ዞን ይዞት የመጣው ዕድል አምልጦን ትውልድ እንዳይወቅሰን መጠንቀቅ አለብን” ብለዋል።አካባቢው የልማት ኮሪደር ቢሆንም ማኅበረሰቡ ከልማት ሳይጠቀም መቆየቱን የገለጹት ዋና አፈ ጉባኤው፣ ኮርፖሬሽኑ ይዞት የመጣውን የልማት ዕድል ለመጠቀም በቁጭት እና በቁርጠኝነት መነሳሳት እንደሚገባ አሳስበው ኮርፖሬሽኑን አመስግነዋል።በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መቱ አኩ፣ በአስተላለፉት መልእክት፣ “ተቋሙ ወደ ምዕራብ ኦሞ ዞን ይዞት የመጣው ዕድል አምልጦን ትውልድ እንዳይወቅሰን መጠንቀቅ አለብን” ብለዋል። አካባቢው የልማት ኮሪደር ቢሆንም ማኅበረሰቡ ከልማት ሳይጠቀም መቆየቱን የገለጹት ዋና አፈ ጉባኤው፣ ኮርፖሬሽኑ ይዞት የመጣውን የልማት ዕድል ለመጠቀም በቁጭት እና በቁርጠኝነት መነሳሳት እንደሚገባ አሳስበው ኮርፖሬሽኑን አመስግነዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ጄነራል አስራት ዴኔሮ በበኩላቸው፣ መከላከያ ሠራዊት ከክልሉ የፀጥታ ኃይል እና ከማኅበረሰቡ ጋር በመሆን ለአካባቢው ዘላቂ ሰላም እና ልማት በጋራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።አክለውም የሰላም ማስቀጠያ አንዱ መሣሪያ ልማት ወደ አካባቢው እንዲመጣ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው ያሉት ጄነራሉ፣ ለዚህም ኮርፖሬሽኑ ወደ አካባቢው ይዞ የመጣውን የልማት ዕድል በእግባቡ መጠቀም እና መደገፍ ከአመራሩ እና ከሕዝቡ እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ ለመሳተፍ ከዞን እና ወረዳ የመጡ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና አርብቶ አደሮች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፣ “እስከዛሬ ሳናውቅ በልማት ወደ ኋላ በመቅረታችን ተጎድተናል፤ አሁን ግን ኮርፖሬሽኑ ይዞ የመጣው የልማት ዕድል ሊያመልጠን አይገባም” ” ካሉ በኋላ “አካባቢያችንን ለመለወጥ ቆርጦ የመጣ የልማት ድርጅት ሲገኝ ከተቋሙ ጎን ተሰልፈን በምንችለው አቅም መደገፍ ይገባል።” በማለት አቋማቸውን አስታውቀዋል።በአለፉት ጊዜያት በርካታ የልማት ዕድሎችን ባለማወቅ ማሳለፋቸውን የአስታወሱት አስተያየት ሰጪዎቹ “አሁን አዲስ ዘመን ነው፤ ይህ ዕድል በፍጹም ሊያመልጠን አይገባም።” በማለት በአጽንዖት ተናግረዋል።በወቅቱ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽንን አጠቃላይ ገጽታን እና የሥራ እንቅስቃሴን የተመለከተ ገለጻ በተቋሙ የኦፕሬሽን ዐቢይ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፈለቀ ገዛኸኝ ቀርቧል።
በዕለቱ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኃላፊ፤ የክልል፣ ዞን እና ወረዳ አመራሮች፣ የማጂና ሱሪ ወረዳዎች የጎሳ መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት እና የጸጥታ ኃይሎች ተገኝተዋል።
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!