በቅርቡ እንደሚመረቅ የሚጠበቀው የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓት እና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ከብዙ በጥቂቱ የሚመለከተውን ይመስላል።
- የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ክትትል እና ድጋፍ ያልተለየው ይህ ማዕከል ከአዲስ አበባ በ470 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዋና ከተማ ቦንጋ በ2.5 ሄክታር ይዞታ ላይ እየተገነባ ነው።
- የግንባታ ማስጀመሪያ የውል ስምምነት እና የፕሮጀክት ሳይት ሰነዶች ርክክብ የካቲት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ተደረገ።
- ከርክክብ በኋላ መጋቢት 2014 ዓ.ም የፕሮጀክቱ ግንባታ በይፋ ተጀመረ።
- ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ባለ አራት ፎቅ ሕንጻ፣ በዓመት ከ150 ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ማዘጋጀት የሚችል የዘር ማበጠሪያ ማሽን መትከያ ቦታ፣ 115 ሺህ ኩንታል የመያዝ አቅም ያሏቸው የግብርና ግብዓት ማከማቻ መጋዘኖች፣ የእርሻ መሣሪያዎችን ማሳያ ክፍል እንዲሁም የላብራቶሪ፣ የቢሮ እና የሌሎች አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ይኖሩታል።
- ለፕሮጀክቱ ግንባታ እስከአሁን 700 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ካፒታል ወጪ ተደርጓል።
- ማዕከሉ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ካለው ጠቀሜታ ባሻገር በአጎራባች ክልሎች እና ከተሞች በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ አርሶና አርብቶ አደሮችን እንዲሁም ባለሃብቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ እና ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!
ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ቦንጋ