ኮርፖሬሽኑ የታማኝ ግብር ከፋይነት የፕላቲነም ደረጃ ሽልማት ተበረከተለት

* በ2016 በጀት ዓመት ከ743 ሚሊየን ብር በላይ ግብር በመክፈል ለሁለተኛ ጊዜ በፕላቲነም ደረጃ ለመሸለም በቅቷል
****
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30/2017 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የታማኝ ግብር ከፋይነት የፕላቲነም ደረጃ ሽልማት ተበረከተለት።
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደ 6ኛው ዙር የ2016 የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋና እና የእውቅና መርሐ ግብር ላይ ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት ከ743 ሚሊየን ብር በላይ ግብር በመክፈል ለሁለተኛ ጊዜ በፕላቲነም ደረጃ ተሽላሚ ሆኗል።
ሽልማቱን ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እጅ የተቀበሉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም ናቸው።በተመሳሳይ ኮርፖሬሽኑ በ5ኛው ዙር የ2015 የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋና እና እውቅና መርሐ ግብር ላይ የፕላቲነም ደረጃ ተሸላሚ በመሆን ዋንጫ ማግኘቱ ይታወሳል።


