Accolades


















“የኮርፖሬሽኑ አምባሳደር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን” ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) የኢኢሆ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
=============================
ሀዋሳ፣ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) የሚመራ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር ማባዣ እርሻዎችን ጎበኘ።
የልዑካን ቡድኑ ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸውን የጎንዴ እና አርዳይታ የምርጥ ዘር ማባዣ እርሻዎች እንዲሁም የኮፈሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዘር ዝግጅትን ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ወቅት የኢኢሆ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልእክት፣ ኮርፖሬሽኑ ግብርናን ለማዘመን እያደረገ ለሚገኘው ጥረት ተቋማቸው አምባሳደር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
አክለውም የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን በማፈላለግ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በሽርክና እንዲሰሩ ኢኢሆ የኢንቨስትመንት እድሎችን እንደሚያመቻችገልጸዋል። ኮርፖሬሽኑ የምርጥ ዘር እርሻዎችን እያስፋፋ እና ትርፋማ እየሆነ በቀጠለ ቁጥር የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያስታወቁት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በተመለከቷቸው የልማት ሥራዎች መደሰታቸውን ገልጸው፣ የኮርፖሬሽኑን ሥራ አመራር እና ሠራተኞች “በርቱ፣ በጣም እንኮራባችኋለን” ብለዋል።









ኮርፖሬሽኑ የታማኝ ግብር ከፋይነት የፕላቲነም ደረጃ ሽልማት ተበረከተለት

* በ2016 በጀት ዓመት ከ743 ሚሊየን ብር በላይ ግብር በመክፈል ለሁለተኛ ጊዜ በፕላቲነም ደረጃ ለመሸለም በቅቷል
****
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30/2017 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የታማኝ ግብር ከፋይነት የፕላቲነም ደረጃ ሽልማት ተበረከተለት።
መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደ 6ኛው ዙር የ2016 የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋና እና የእውቅና መርሐ ግብር ላይ ኮርፖሬሽኑ በ2016 በጀት ዓመት ከ743 ሚሊየን ብር በላይ ግብር በመክፈል ለሁለተኛ ጊዜ በፕላቲነም ደረጃ ተሽላሚ ሆኗል።
ሽልማቱን ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እጅ የተቀበሉት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም ናቸው።በተመሳሳይ ኮርፖሬሽኑ በ5ኛው ዙር የ2015 የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋና እና እውቅና መርሐ ግብር ላይ የፕላቲነም ደረጃ ተሸላሚ በመሆን ዋንጫ ማግኘቱ ይታወሳል።



ADVERTISEMENT
Ethiopian Agricultural Business Corporation
Tender Number: EABC/DAP/001/IR03/2025
P.O.Box 100077
Tel: 011-4 425623/011-4425629
Fax: 011-4 425655/011-4 425622
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation, Agricultural Inputs Supply Sector Akaki – Kality Sub – City Wereda 06, On or before 10:00 A.M on October 28/2024 and must be accompanied by the aforementioned bid security.
ETHIOPIAN AGRICULTURAL BUSSINESS CORPORATION
ADDIS ABABA ETHIOPIA
* ለተጠቃሚዎች የሚሰጠውን የአዲስ እርሻ መሬት ዝግጅት አገልግሎት ለማስፋትም ዶዘሮች እና ኤክስካቬተር አስገብቷል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከመሬት ዝግጅት እስከ ጎተራ ድረስ የሜካናይዜሽን አገልግሎት የሚሰጡ ዎኪንግ ትራክተሮችን አስመጣ፡፡20 የፈረስ ጉልበት ያላቸው እነዚህ ትራክተሮች የቻይና ስሪት ሲሆኑ፣ በኮርፖሬሽኑ ባለሞያዎች ተገጣጥመዋል፡
፡የኮርፖሬሽኑ የእርሻ መሣሪያዎች አቅርቦት እና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ክፍሌ እንደገለጹት፣ ትራክተሮቹ ለሰፋፊ የእርሻ መሬቶች እና ለአነስተኛ ማሳዎች ያገለግላሉ።
ለተጠቃሚዎች የሚቀርቡት እነዚህ ትራክተሮች የግብርና ሥራን ዘመናዊ እና ቀላል የሚያደርጉ፣ የአርሶ አደሩን ጉልበት የሚቆጥቡ እና ከበሬ ጫንቃ የሚያላቅቁ መሆናቸውን አቶ መንግሥቱ አስረድተዋል፡፡

ትራክተሮቹ ማረስ፣ መከስከስ፣ መዝራት፣ ማጨድ እንዲሁም ምርት፣ ዘር፣ አግሮኬሚካል እና ማዳበሪያ ማጓጓዝ፣ ውሃ ማጠጣት እና ሌሎችንም አገልግሎቶች መስጠት ይችላሉ።በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ ለተጠቃሚዎች የሚሰጠውን የአዲስ እርሻ መሬት ዝግጅት አገልግሎት ለማስፋት ዶዘሮች እና ኤክስካቬተር ከውጭ ማስገባቱን አቶ መንግሥቱ አስታውቀዋል፡፡
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!








