አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢግሥኮ):- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2016/17 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ግዥ፣ አቅርቦት እና ሥርጭት እንዲሳለጥ ለአበረከተው የጎላ አስተዋጽዖ ከግብርና ሚኒስቴር የእውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት እና ዋንጫ ተበረከተለት።
በተመሳሳይ የኮርፖሬሽኑ የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ገብሬ መላክ የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ ሂደቱ እንዲሳለጥ እና ለተጠቃሚዎች በወቅቱ እንዲደርስ ለአበረከቱት የጎላ አስተዋጽዖ የእውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶአቸዋል።
አዲስ አበባ በሚገኘው የኃይሌ ሪዞርት ሆቴል ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በግብርና ሚኒስቴር በተዘጋጀው የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር ላይ ኮርፖሬሽኑ እና አቶ ሰለሞን ገብሬ ከግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!