አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሥራ መሪዎች እና ሠራተኞች በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተወያዩ።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም የኮርፖሬሽኑ የሥራ መሪዎች እና ሠራተኞች ባደረጉት ሁለገብ ጥረት ተቋሙ በ2016 በጀት ዓመት ያቀዳቸውን ሥራዎች ማሳካት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለተገኘው ውጤት የሥራ መሪዎችን እና ሠራተኞችን አመስግነው፣ በተያዘው በጀት ዓመት በከፍተኛ ቁርጠኝነት በመስራት የኮርፖሬሽኑን ስኬታማ ጉዞ እንዲያስቀጥሉ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡አክለውም በተፈጥሮ ሙጫ ምርቶች አቅርቦት፣ በመሬት ዝግጅት፣ በሰብል መሰብሰብ፣ በተሽከርካሪዎች ጥገና ጥራት እና በፕሮጀክቶች አፈጻጸም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡የምርት እና አገልግሎት አይነትና መጠንን ማስፋት እና ወጪ ቅነሳ ሌሎች የበጀት ዓመቱ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስገንዝበዋል፡፡በዕለቱ ከሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ዋና ሥራ አስፈጻሚው እና ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!