* ቋሙ ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ተጠቁሟል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢግሥኮ)፦ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ጥሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) ገለጸ።
የኮርፖሬሽኑ አፈጻጸም ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በተገመገመበት ወቅት የውይይት መድረኩን የመሩት የኢኢሆ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያስመዘገበው አፈጻጸም ጥሩ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ኮርፖሬሽኑ ውጤቱን አስጠብቆ ለመቀጠል ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።ለአብነትም ምርጥ ዘር እና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የሰብል ምርቶች ላይ በስፋት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ለዚህ ደግሞ የኢኢሆ ድጋፍ እንደማይለይ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል።የኢኢሆ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መልእክት ሳህሉ በበኩላቸው፣ የኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር ኢኢሆ የሚሰጣቸውን ግብረ መልሶች ተቀብሎ በዕቅዱ ውስጥ በማካተት በየጊዜው የአፈጻጸም ሪፖርት ማቅረቡን አድንቀው፣ ሚዛናዊ የውጤት ተኮር ሥርዓትን (BSC) በትክክል የሚተገብር ተቋም መሆኑንም መስክረዋል።በዕለቱ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሥራ ኃላፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም እና የሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ወልደአብ ደምሴ ምላሽ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2016 በጀት ዓመት ከኦፕሬሽን ሥራዎች እና ከልዩ ልዩ ገቢዎች 10.12 ቢሊዮን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን፣ በትርፍ ረገድም ከታክስ በፊት ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገብ ችላል፡፡በተመሳሳይ በውጤት ተኮር አራቱ ዕይታዎች አንጻር 93.3 በመቶኛ በማከናወን ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ነው፡፡
###
ግብርናን ማዘመን ግባችን ነው!