አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ኢግሥኮ):-የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በአንድ ጀንበር 600 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የተላለፈውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትለው ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።በዕለቱ በተደረገ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ጠቀሜታ ያላቸው የጥላ ዛፍ ችግኞች በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት እና በቅርንጫፎች ተተክለዋል።በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም በአስተላለፉት መልእክት፣ በየዓመቱ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ እና የጥላ ዛፍ ችግኞችን በዋና መ/ቤት እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንደሚተክሉ አስታውሰው፣ ዛሬም ከጠዋት ጀምሮ
አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሐ ግብር እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።”ከተቋሙ ተልእኮ አኳያ ምድሪቷን አረንጓዴ በማልበስ ሥራ እንታወቃለን” ያለት አቶ ክፍሌ፣ እንደአለፋት ዓመታት ሁሉ ለተተከሉ ችግኞች በመደረግ ላይ ያለው እንክብካቤ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
###
ምድሪቱን አረንጓዴ በማልበስ ለምንታወቀው የኢግሥኮ የሥራ መሪዎች እና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራን ማኖር የዕለት ተዕለት ተግባራችን ነው።